የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb17 ሐምሌ ገጽ 8
  • ከቤት ወደ ቤት ስናገለግል መልካም ምግባር ማሳየት

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ከቤት ወደ ቤት ስናገለግል መልካም ምግባር ማሳየት
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2017
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በር ላይም ሆነ በስልክ የምናስጠናቸው ሰዎች እድገት እንዲያደርጉ መርዳት
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2006
  • በአገልግሎት ረገድ ክህሎታችንን ማዳበር—ከአምላክ የተላከ ምሥራች! የተባለውን ብሮሹር ተጠቅሞ በር ላይ እንደቆሙ ጥናት ማስጀመር
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2015
  • ሰዎችን በራቸው ላይ እንደቆምን አሊያም በስልክ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ማስጀመር
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2005
  • ሥርዓታማነት—ለአምላክ ያደሩ ሰዎች መለያ
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2001
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2017
mwb17 ሐምሌ ገጽ 8

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ከቤት ወደ ቤት ስናገለግል መልካም ምግባር ማሳየት

አንድ ወንድም ከቤት ወደ ቤት በሚያገለግልበት ወቅት በመስኮት አጮልቆ ሲመለከት እንዲሁም ብስኩት ሲበላ፤ ሌላኛው ወንድም ደግሞ የጽሑፍ መልእክት ሲልክ

ክርስቲያኖች ለዓለም እንደ “ትርዒት” ናቸው። (1ቆሮ 4:9) በመሆኑም፣ አንዳንድ የቤት ባለቤቶች በመስኮት ቢመለከቱን ወይም ከበራቸው ጀርባ ቆመው ቢያዳምጡን ሊያስገርመን አይገባም። እንዲያውም የምናንኳኳው ቤት የምናደርገውን ነገር ለማየት፣ ለመስማትና ለመቅዳት የሚያስችል የደህንነት ካሜራና ማይክሮፎን የተገጠመለት ሊሆን ይችላል። ከቤት ወደ ቤት ስናገለግል መልካም ምግባር ማሳየት የምንችልባቸው አንዳንድ መንገዶች ከዚህ በታች ቀርበዋል።—2ቆሮ 6:3

በድርጊታችን (ፊልጵ 1:27)፦

  • ቤታቸውን አጮልቀን ለማየት ባለመሞከር የግለሰቦቹን ነፃነት እንደምናከብር እናሳይ። በሩ ላይ ቆመን መብላት፣ መጠጣት፣ ስልክ መደወል ወይም የጽሑፍ መልእክት መላክ የለብንም

በንግግራችን (ኤፌ 4:29)፦

  • በሩ እስኪከፈት ስንጠብቅ የቤቱ ባለቤት አጠገባችን ቢሆን የማንናገረውን ምንም ነገር መናገር የለብንም። እንዲያውም አንዳንድ አስፋፊዎች የቤቱ ባለቤት በሩን እስኪከፈትላቸው ድረስ ከአገልግሎት ጓደኛቸው ጋር የሚያደርጉትን ጭውውት ያቆማሉ፤ ይህም ቀጥሎ የሚናገሩትን ለመዘጋጀት ያስችላቸዋል

አገልግሎት ላይ ያሉ ሁለት ወንድሞች የቤቱ ባለቤት በሩን እስኪከፍትላቸው ሥርዓት ባለው ሁኔታ ሲጠብቁት፤ የቤቱ ባለቤት ደግሞ በበሩ ቀዳዳ ሲያያቸው

ከቤት ወደ ቤት ስናገለግል መልካም ምግባር ማሳየት የምንችልባቸው ምን ሌሎች መንገዶች አሉ?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ