ክርስቲያናዊ ሕይወት
ንጹሑን አምልኮ ከፍ አድርገህ የምትመለከተው ለምንድን ነው?
በምርኮ የነበሩት አይሁዳውያን ሕዝቅኤል በራእይ ስላየው ቤተ መቅደስ መስማታቸው አጽናንቷቸዋል፤ ምክንያቱም ይህ ራእይ፣ ንጹሑ አምልኮ መልሶ እንደሚቋቋም ተስፋ ሰጥቷቸዋል። በምንኖርበት በዚህ የመጨረሻ ዘመን ንጹሑ አምልኮ “ከተራሮች አናት በላይ ጸንቶ [ቆሟል]”፤ ወደዚያ ከጎረፉት ከሁሉም ብሔራት የተውጣጡ ሰዎች መካከል እኛም እንገኝበታለን። (ኢሳ 2:2) ይሖዋን ማወቅና እሱን ማገልገል መቻልህ ምን ያህል ታላቅ ክብር እንደሆነ አዘውትረህ ታሰላስላለህ?
ንጹሑ አምልኮ የሚያስገኛቸው በረከቶች፦
በአእምሯችን ውስጥ ለሚጉላሉ ጥያቄዎች መልስ ለማግኘት የሚያስችለን የተትረፈረፈ መንፈሳዊ ምግብ፣ ልንመራባቸው የሚገቡ ጠቃሚ ምክሮች እንዲሁም የተረጋገጠ ተስፋ።—ኢሳ 48:17, 18፤ 65:13፤ ሮም 15:4
ችግር በሚደርስብን ጊዜ ብርታት የሚሰጠን “የአምላክ ሰላም።”—ፊልጵ 4:6, 7
ንጹሕ ሕሊና።—2ጢሞ 1:3
“ከይሖዋ ጋር የጠበቀ ወዳጅነት።”—መዝ 25:14
ንጹሑን አምልኮ ከፍ አድርጌ እንደምመለከት ማሳየት የምችለው በየትኞቹ መንገዶች ነው?