ክርስቲያናዊ ሕይወት
ሕይወታችሁን ይሖዋን ለማወደስ ተጠቀሙበት!
ሕይወት ውድ ስጦታ ነው። ይህን ስጦታ በየዕለቱ የምንጠቀምበት መንገድ ለስጦታው ምን ያህል አድናቆት እንዳለን ያሳያል። የይሖዋ ምሥክሮች እንደመሆናችን መጠን ተሰጥኦዋችንንና ችሎታችንን የሕይወት ምንጭ የሆነውን ይሖዋን ለማክበርና ከፍ ከፍ ለማድረግ ልንጠቀምበት እንፈልጋለን። (መዝ 36:9፤ ራእይ 4:11) ይሁንና ክፋት በሞላበት በዚህ ዓለም ውስጥ ስንኖር በየዕለቱ የሚያጋጥመን የኑሮ ውጣ ውረድ ሳይታወቀን መንፈሳዊ ነገሮችን ችላ እንድንል ሊያደርገን ይችላል። (ማር 4:18, 19) በመሆኑም እያንዳንዳችን እንደሚከተለው ብለን ራሳችንን መጠየቃችን ተገቢ ነው፦ ‘በእርግጥ ለይሖዋ ምርጤን እየሰጠሁ ነው? (ሆሴዕ 14:2) ሥራዬ ለይሖዋ በማቀርበው አገልግሎት ላይ ተጽዕኖ እያሳደረብኝ ነው? ምን መንፈሳዊ ግቦች አሉኝ? አገልግሎቴን ይበልጥ ማስፋት የምችለው እንዴት ነው?’ በእነዚህ መስኮች ማሻሻያ ማድረግ እንዳለብህ ካስተዋልክ ይሖዋ እንዲረዳህ ከመጸለይና አስፈላጊውን ማስተካከያ ከማድረግ ወደኋላ አትበል። ይሖዋን በየዕለቱ ማወደስ አስደሳችና አርኪ ሕይወት ለመምራት እንደሚያስችለን ምንም ጥርጥር የለውም!—መዝ 61:8
ተሰጥኦህን እየተጠቀመበት ያለው ይሖዋ ነው ወይስ የሰይጣን ዓለም?
ተሰጥኦዋችሁን ይሖዋን ለማገልገል ተጠቀሙበት የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
ተሰጥኦህን የሰይጣን ዓለም እንዲጠቀምበት ማድረግ ጥበብ የጎደለው አካሄድ የሆነው ለምንድን ነው? (1ዮሐ 2:17)
ምርጣቸውን ለይሖዋ የሚሰጡ ሰዎች ምን በረከቶች ያገኛሉ?
ባለህ ተሰጥኦና ሙያ ተጠቅመህ በየትኞቹ የቅዱስ አገልግሎት ዘርፎች ልትካፈል ትችላለህ?