ክርስቲያናዊ ሕይወት
እውነተኛ ፍቅር ምንድን ነው?
ይሖዋ ጋብቻን ያቋቋመው በአንድ ወንድና በአንዲት ሴት መካከል የሚፈጸም ዘላቂ ጥምረት እንዲሆን አስቦ ነው። (ዘፍ 2:22-24) ፍቺ የሚፈቀደው የፆታ ብልግና ከተፈጸመ ብቻ ነው። (ሚል 2:16፤ ማቴ 19:9) ይሖዋ ትዳር ደስታ የሰፈነበት እንዲሆን ስለሚፈልግ ጥሩ የትዳር ጓደኛ ለመምረጥና ትዳርን አስደሳች ለማድረግ የሚረዱ መሠረታዊ ሥርዓቶችን ለክርስቲያኖች ሰጥቷቸዋል።—መክ 5:4-6
እውነተኛ ፍቅር ምንድን ነው? የተባለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
ፍራንክና ቦኒ ለልጃቸው ለሊዝ የሰጧት ምክር ጥበብና ፍቅር የተንጸባረቀበት ነው የምንለው ለምንድን ነው?
እየተጠናናችሁ ያላችሁትን ሰው እለውጠዋለሁ ብሎ ማሰብ ስህተት የሆነው ለምንድን ነው?
ፖልና ፕሪሲላ ለሊዝ ምን ጥበብ የተንጸባረቀበት ምክር ሰጧት?
በዛክና በሜጋን ትዳር ውስጥ ችግሮች የተከሰቱት ለምንድን ነው?
ጆንና ሊዝ ምን ተመሳሳይ መንፈሳዊ ግቦች ነበሯቸው?
ከአንድ ሰው ጋር የጋብቻ መሃላ ከመፈጸማችሁ በፊት የግለሰቡን “የተሰወረ የልብ ሰው” ማወቅ ያለባችሁ ለምንድን ነው? (1ጴጥ 3:4)
እውነተኛ ፍቅር ምንድን ነው? (1ቆሮ 13:4-8)