ክርስቲያናዊ ሕይወት
አትጨነቁ
ኢየሱስ በተራራው ስብከት ላይ “ስለ ሕይወታችሁ . . . አትጨነቁ” ብሏል። (ማቴ 6:25) በሰይጣን ዓለም ውስጥ የምንኖር ፍጽምና የጎደለን ሰዎች እንደመሆናችን መጠን አልፎ አልፎ መጨነቃችን አይቀርም፤ ይሁንና ኢየሱስ፣ ተከታዮቹ ከልክ በላይ መጨነቅ እንደሌለባቸው አስተምሯል። (መዝ 13:2) ለምን? ምክንያቱም ስለማንኛውም ነገር ሌላው ቀርቶ በየዕለቱ ስለሚያስፈልጉን ነገሮችም እንኳ ከልክ በላይ የምንጨነቅ ከሆነ ትኩረታችን ሊከፋፈልና መንግሥቱን ማስቀደም ከባድ ሊሆንብን ይችላል። (ማቴ 6:33) ኢየሱስ ቀጥሎ የተናገረው ሐሳብ አላስፈላጊ ጭንቀትን እንድናስወግድ ይረዳናል።
ማቴ 6:26—ወፎችን በመመልከት ምን እንማራለን? (w16.07 9-10 አን. 11-13)
ማቴ 6:27—ከልክ ያለፈ ጭንቀት ጊዜንና ጉልበትን ከማሟጠጥ ውጪ የሚፈይደው ነገር የለም የምንለው ለምንድን ነው? (w05 11/1 22 አን. 5)
ማቴ 6:28-30—የሜዳ አበቦችን በመመልከት ምን እንማራለን? (w16.07 10-11 አን. 15-16)
ማቴ 6:31, 32—ክርስቲያኖች ከአሕዛብ የሚለዩት በምንድን ነው? (w16.07 11 አን. 17)
ስለ የትኞቹ ጉዳዮች መጨነቄን ማቆም እፈልጋለሁ?