ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዮሐንስ 3-4
ኢየሱስ ለአንዲት ሳምራዊት ሴት መሠከረ
ኢየሱስን መደበኛ ባልሆነ መንገድ እንዲመሠክር ያስቻለው ምንድን ነው?
4:7—ውይይቱን የጀመረው ስለ አምላክ መንግሥት በመናገር ወይም መሲሕ እንደሆነ በመግለጽ ሳይሆን ሴትየዋ ውኃ እንድትሰጠው በመጠየቅ ነው
4:9—በዘሯ ምክንያት ስለ ሳምራዊቷ ሴት አሉታዊ አመለካከት አላደረበትም
4:9, 12—ሴትየዋ ሊያወዛግቡ የሚችሉ ጉዳዮችን ብታነሳም ኢየሱስ ውይይቱ መስመሩን እንዳይስት አድርጓል።—cf ገጽ 77 አን. 3
4:10—ከሴትየዋ የዕለት ተዕለት ሕይወት ጋር የተያያዘ ምሳሌ በመጠቀም ውይይቱን ጀምሯል
4:16-19—ሥነ ምግባር የጎደለው ሕይወት የምትመራ ቢሆንም ኢየሱስ በአክብሮት አነጋግሯታል
ይህ ዘገባ መደበኛ ባልሆነ መንገድ የመመሥከርን አስፈላጊነት የሚያሳየው እንዴት ነው?