ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዮሐንስ 5-6
በትክክለኛ የልብ ዝንባሌ ተነሳስታችሁ ኢየሱስን ተከተሉ
ኢየሱስ ለመረዳት ከባድ የሆነ ሐሳብ በተናገረበት ወቅት ከደቀ መዛሙርቱ መካከል አንዳንዶቹ ተሰናክለው እሱን መከተል አቆሙ። ከአንድ ቀን በፊት ኢየሱስ እነዚህን ሰዎች ተአምራዊ በሆነ መንገድ መግቧቸው ነበር፤ ይህም አምላክ ኃይል እንደሰጠው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ነው። ታዲያ እነዚህ ሰዎች የተሰናከሉት ለምንድን ነው? ከሁኔታዎች መረዳት እንደሚቻለው ኢየሱስን የተከተሉት ከራስ ወዳድነት በመነጨ ፍላጎት ተነሳስተው ማለትም ቁሳዊ ጥቅም ማግኘት ፈልገው ነበር።
እያንዳንዳችን ራሳችንን እንደሚከተለው በማለት መጠየቅ አለብን፦ ‘ኢየሱስን የምከተለው ለምንድን ነው? በዋነኝነት እንዲህ የማደርገው አሁንም ሆነ ወደፊት በረከት ስለሚያስገኝልኝ ነው? ወይስ ይሖዋን ስለምወደውና ላስደስተው ስለምፈልግ ነው?’
በዋነኝነት ይሖዋን የምናገለግለው በሚከተሉት ምክንያቶች ከሆነ ልንሰናከል የምንችለው ለምንድን ነው?
ከአምላክ ሕዝቦች ጋር መሆን ስለሚያስደስተን
ገነት ውስጥ መኖር ስለምንፈልግ