ክርስቲያናዊ ሕይወት
ፍቅር የእውነተኛ ክርስቲያኖች መለያ ነው—ውድ የሆነውን አንድነታችንን ጠብቁ
አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ኢየሱስ ከመሞቱ በፊት በነበረው ምሽት ላይ፣ ደቀ መዛሙርቱ “ፍጹም አንድነት እንዲኖራቸው” ጸልዮአል። (ዮሐ 17:23 ግርጌ) አንድነታችንን ጠብቀን ለመኖር እንድንችል ፍቅር ማሳየት ያስፈልገናል፤ ፍቅር ደግሞ “የበደል መዝገብ የለውም።”—1ቆሮ 13:5
ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?
የይሖዋን ምሳሌ በመከተል በሌሎች መልካም ጎን ላይ አተኩር
በነፃ ይቅር በል
ከሌሎች ጋር የተፈጠረው አለመግባባት ከተፈታ በኋላ ጉዳዩን ደግመህ አታንሳው።—ምሳሌ 17:9
“እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ”—የበደል መዝገብ አይኑራችሁ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
በቪዲዮው የመጀመሪያ ክፍል ላይ፣ ሄለን ‘የበደል መዝገብ’ እንዳላት ያሳየችው እንዴት ነው?
በቪዲዮው ሁለተኛ ክፍል ላይ፣ ሄለን የነበራትን አሉታዊ አስተሳሰብ አስወግዳ አዎንታዊ አመለካከት የያዘችው እንዴት ነው?
ሄለን ለጉባኤው አንድነት አስተዋጽኦ ያደረገችው እንዴት ነው?
የበደል መዝገብ የምንይዝ ከሆነ የበለጠ የሚጎዳው ማን ነው?