የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w21 የካቲት ገጽ 25
  • የማረካቸው ፈገግታ ነው!

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የማረካቸው ፈገግታ ነው!
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2021
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ከጉብዝናችን ወራት ጀምሮ ፈጣሪያችንን ማሰብ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2000
  • በጋሪ የሚሰጥ ምሥክርነት በዓለም ዙሪያ ያስገኘው ውጤት
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2018
  • ፍቅር የእውነተኛ ክርስቲያኖች መለያ ነው—ውድ የሆነውን አንድነታችንን ጠብቁ
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2018
  • ፈገግታ—ብዙ ጥቅም ያስገኝልሃል!
    ንቁ!—2000
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2021
w21 የካቲት ገጽ 25

የማረካቸው ፈገግታ ነው!

ሄለን የጽሑፍ ጋሪው አጠገብ ፈገግ ብላ ቆማለች። ሁለት ሴቶች በዚያ እያለፉ ነው።

የፊሊፒንስ ከተማ በሆነችው በባጊዮ ሲቲ ባለ የንግድ አካባቢ፣ ሁለት ወጣት ሴቶች በእግራቸው እየሄዱ ነው። እየሄዱ ሳለ የምሥክርነት መስጫ ጋሪ ተመለከቱ፤ ሆኖም ወደዚያ ለመቅረብ አላሰቡም። ከጋሪው አጠገብ የቆመችው ሄለን የተባለችው እህት ሞቅ ያለ ፈገግታ አሳየቻቸው። ሴቶቹ መንገዳቸውን ቀጠሉ፤ ሆኖም ሄለን ያሳየቻቸው ሞቅ ያለ ፈገግታ ትኩረታቸውን ስቦት ነበር።

በኋላ ላይ ሴቶቹ አውቶብስ ተሳፍረው ወደ ቤታቸው ሲሄዱ በአንድ የስብሰባ አዳራሽ ላይ ትልቅ የ⁠jw.org ምልክት ተለጥፎ አዩ። ይህን ምልክት ቀደም ሲል በምሥክርነት መስጫ ጋሪው ላይ እንዳዩት አስታወሱ። ሁለቱም ከአውቶብሱ ወርደው ወደ ስብሰባ አዳራሹ ሄዱ፤ እዚያም መግቢያው ላይ የተለያዩ ጉባኤዎች ስብሰባ የሚያደርጉበትን ፕሮግራም ተመለከቱ።

እነዚያው ሴቶች ሄለንን የስብሰባ አዳራሹ ውስጥ ሲያዩአት ፈገግ ብለው ወደ እሷ እየመጡ።

ሁለቱ ሴቶች በአንደኛው የጉባኤ ስብሰባ ላይ ተገኙ። ስብሰባ አዳራሹ ውስጥ ማንን ቢያገኙ ጥሩ ነው? ሄለንን! ያኔ ሞቅ ያለ ፈገግታ ያሳየቻቸው ሴት እንደሆነች ለመለየት ጊዜ አልፈጀባቸውም። ሄለን እንዲህ ብላለች፦ “ወደ እኔ ሲመጡ ሳያቸው ትንሽ ግራ ተጋብቼ ነበር። ምን አድርጌያቸው ይሆን ብዬ አስቤ ነበር።” ሴቶቹ ግን የተፈጠረውን ነገር ለሄለን ነገሯት።

ወጣቶቹ በስብሰባው እንዲሁም ከወንድሞችና ከእህቶች ጋር ባሳለፉት ጊዜ በጣም ተደሰቱ፤ እንግድነት አልተሰማቸውም። ሌሎች አዳራሹን ሲያጸዱ ሲያዩ እነሱም ማገዝ ይችሉ እንደሆነ ጠየቁ። ከዚያ ወዲህ አንደኛዋ ወጣት ከአገር ብትወጣም ሌላኛዋ ወጣት በስብሰባዎች ላይ መገኘትና መጽሐፍ ቅዱስን ማጥናት ጀምራለች። እንግዲህ ይህ ውጤት የተገኘው እህት ባሳየችው ፈገግታ የተነሳ ነው!

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ