ክርስቲያናዊ ሕይወት
በጋሪ የሚሰጥ ምሥክርነት በዓለም ዙሪያ ያስገኘው ውጤት
የሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 5 እንደሚገልጸው በመጀመሪያው መቶ ዘመን የነበሩ ክርስቲያኖች ምሥራቹን ለሰዎች ለመስበክ ሲሉ ብዙዎች ወደሚገኙበት ቦታ ይኸውም ወደ ቤተ መቅደሱ ሄደዋል። (ሥራ 5:19-21, 42) በዛሬው ጊዜም ብዙ ሰዎች በሚገኙበት አካባቢ በጋሪ የሚሰጠው ምሥክርነት ጥሩ ውጤት አስገኝቷል።
በጋሪ የሚሰጥ ምሥክርነት በዓለም ዙሪያ ያስገኘው ውጤት የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
በጋሪ ተጠቅሞ ምሥክርነት መስጠት የተጀመረው መቼና እንዴት ነው?
በጠረጴዛ ተጠቅሞ ከመመሥከር ይልቅ በጋሪ አማካኝነት መመሥከር ምን ጥቅሞች አሉት?
ከሚ ጆንግ ዩ ተሞክሮ ምን እንማራለን?
የሃኮብ ሰሎሜ ተሞክሮ በጋሪ ተጠቅሞ መመሥከር የሚያስገኘውን ጥቅም የሚያሳየው እንዴት ነው?
የአኒስና የባለቤቷ ተሞክሮ በጋሪ አማካኝነት ውጤታማ በሆነ መንገድ መመሥከር ስለሚቻልበት መንገድ ምን ያስተምረናል?