ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዮሐንስ 20-21
“ከእነዚህ አስበልጠህ ትወደኛለህ?”
በጥንት ዘመን የነበሩ ዓሣ አጥማጆች ውጤታማ ለመሆንና የልፋታቸውን ፍሬ ለማግኘት ትዕግሥተኛ፣ ታታሪ እንዲሁም ችግሮችን ለመጋፈጥ ፈቃደኞች መሆን ነበረባቸው። (w12 8/1 18-20) ጴጥሮስ፣ ሰው አጥማጅ ሆኖ ሲሠራ ውጤታማ እንዲሆን እነዚህ ባሕርያት ያስፈልጉታል። ሆኖም ጴጥሮስ፣ ከሚወደው ሰብዓዊ ሥራው እና የኢየሱስን ተከታዮች በመንፈሳዊ ከመመገቡ ሥራ የትኛውን እንደሚያስቀድም መወሰን ያስፈልገው ነበር።
አንተስ የአምላክን መንግሥት ለማስቀደም ስትል በሕይወትህ ውስጥ ምን ማስተካከያዎች አድርገሃል?