የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb19 ሚያዝያ ገጽ 8
  • መለኮታዊውን ትምህርት ተከታተሉ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መለኮታዊውን ትምህርት ተከታተሉ
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2019
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የመንግሥቱን አገልጋዮች ማሠልጠን
    የአምላክ መንግሥት እየገዛ ነው!
  • የይሖዋ ምሥክሮች አገልግሎታቸውን ለማከናወን የሚሠለጥኑት እንዴት ነው?
    ስለ ይሖዋ ምሥክሮች ብዙ ጊዜ የሚነሱ ጥያቄዎች
  • በመንግሥቱ ወንጌላውያን ትምህርት ቤት መማር ትፈልጋለህ?
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2020
  • በመንግሥቱ ወንጌላውያን ትምህርት ቤት ለመማር ማመልከት
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2022
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2019
mwb19 ሚያዝያ ገጽ 8

ክርስቲያናዊ ሕይወት

መለኮታዊውን ትምህርት ተከታተሉ

አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ታላቅ አስተማሪ የሆነው ይሖዋ ከሁሉ የላቀ ትምህርት አዘጋጅቶልናል። የተሻለ ሕይወት ለመምራት የሚያስችለን እንዲሁም አስደናቂ የወደፊት ሕይወት ለማግኘት የሚረዳን ትምህርት በነፃ አቅርቦልናል! (ኢሳ 11:6-9፤ 30:20, 21፤ ራእይ 22:17) ከይሖዋ የምንቀስመው መለኮታዊ ትምህርት፣ ሕይወት አድን የሆነውን መልእክት ለሌሎች ለማካፈልም ያሠለጥነናል።—2ቆሮ 3:5

ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?

  • ትሕትናን እና የዋህነትን አዳብሩ።—መዝ 25:8, 9

  • ይሖዋ በአሁኑ ወቅት ከሚሰጠን ሥልጠና ለመጠቀም ጥረት አድርጉ፤ ለምሳሌ በሳምንቱ መካከል በሚደረገው ስብሰባ ላይ የተማሪ ክፍል ማቅረብ ትችላላችሁ

  • ልትደርሱባቸው የምትችሉ መንፈሳዊ ግቦች አውጡ።—ፊልጵ 3:13

  • ተጨማሪ ሥልጠናዎች ለማግኘት ብቃቱን እንድታሟሉ በሕይወታችሁ ውስጥ አንዳንድ ማስተካከያዎችን አድርጉ።—ፊልጵ 3:8

ከይሖዋ በመማር መንፈሳዊ ብልጽግና ማግኘት የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • አንዳንድ አስፋፊዎች በመንግሥቱ ወንጌላውያን ትምህርት ቤት ለመካፈል ሲሉ የትኞቹን እንቅፋቶች መወጣት አስፈልጓቸዋል?

  • በመንግሥቱ ወንጌላውያን ትምህርት ቤት የሚካፈሉ ተማሪዎች ምን ጥቅሞች ያገኛሉ?

  • ተመራቂዎቹ በአዲሱ የአገልግሎት ምድባቸው ሲያገለግሉ የጉባኤያቸው አባላት የረዷቸው እንዴት ነው?

  • በመንግሥቱ ወንጌላውያን ትምህርት ቤት ለመካፈል መሟላት የሚያስፈልጋቸው ብቃቶች የትኞቹ ናቸው? (kr 189)

  • በይሖዋ ድርጅት ውስጥ ልታገኛቸው የምትችላቸው ምን ሌሎች ሥልጠናዎች አሉ?

ከመንግሥቱ ወንጌላውያን ትምህርት ቤት የተመረቁ ክርስቲያኖች በናሚቢያ፣ በኖርዌይ፣ በዩናይትድ ስቴትስ እንዲሁም በጃፓን ሲያገለግሉ

መለኮታዊውን ትምህርት መከታተልህ ምን በረከቶች ያስገኝልሃል?

በየትኞቹ ቲኦክራሲያዊ ትምህርት ቤቶች ሥልጠና አግኝተሃል?

  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን

  • የአቅኚነት አገልግሎት ትምህርት ቤት

  • የመንግሥት አገልግሎት ትምህርት ቤት

  • የጉባኤ ሽማግሌዎች ትምህርት ቤት

  • የመንግሥቱ ወንጌላውያን ትምህርት ቤት

በየትኞቹ ቲኦክራሲያዊ ትምህርት ቤቶች የመሠልጠን ግብ አለህ?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ