ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዕብራውያን 12-13
ተግሣጽ—የይሖዋ ፍቅር መግለጫ
“ተግሣጽ” የሚለው ቃል ቅጣትን፣ እርማትን፣ መመሪያ መስጠትንና ትምህርትን ያመለክታል። አፍቃሪ የሆነ አባት ልጆቹን እንደሚገሥጽ ሁሉ ይሖዋም ይገሥጸናል። በሚከተሉት መንገዶች ተግሣጽ እናገኛለን፦
መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብ፣ የግል ጥናት ስናደርግ፣ ስብሰባዎች ላይ ስንገኝ እና ስናሰላስል
የእምነት ባልንጀራችን ምክር ወይም እርማት ሲሰጠን
የሠራነው ስህተት ያስከተለብንን ውጤት ስንመለከት
በፍርድ ኮሚቴ ወቀሳ ሲሰጠን ወይም ከጉባኤ ስንወገድ
ይሖዋ ፈተና ወይም ስደት እንዲደርስብን ሲፈቅድ።—w15 9/15 21 አን. 13፤ it-1 629