ክርስቲያናዊ ሕይወት
የተዋጣለት ሠራተኛ ሁን
አንድ የተዋጣለት አናጺ መሣሪያዎቹን እንዴት መጠቀም እንዳለበት ያውቃል። በተመሳሳይም “ምንም የሚያፍርበት ነገር [የሌለው] ሠራተኛ” በማስተማሪያ መሣሪያዎቻችን ውስጥ ያሉትን መሣሪያዎች እንዴት መጠቀም እንዳለበት ያውቃል። (2ጢሞ 2:15) በአገልግሎት ላይ ከምንጠቀምባቸው መሣሪያዎች መካከል የአንዳንዶቹን አጠቃቀም ምን ያህል ጠንቅቀህ እንደምታውቅ ለመገምገም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር።
አምላክን ስማ የዘላለም ሕይወት ታገኛለህ
ይህ ጽሑፍ የተዘጋጀው ለማን ነው?—mwb17.03 5 አን. 1-2
መጽሐፍ ቅዱስን ለማስጠናት ልትጠቀምበት የምትችለው እንዴት ነው?—km 7/12 3 አን. 6
የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪህ ለጥምቀት ብቁ እንዲሆን ለመርዳት ከዚህ ጽሑፍ በተጨማሪ የትኛውን ጽሑፍ መጠቀም ያስፈልግሃል?—km 7/12 3 አን. 7
ከአምላክ የተላከ ምሥራች!
ይህ ጽሑፍ ከሌሎች የማስጠኛ ጽሑፎች የሚለየው እንዴት ነው?—km 3/13 6-7 አን. 3-5
ይህን ጽሑፍ ስታበረክት ምን ለማድረግ መሞከር ይኖርብሃል?—km 9/15 3 አን. 1
ይህን ጽሑፍ ተጠቅመህ መጽሐፍ ቅዱስን ማስጠናት የምትችለው እንዴት ነው?—mwb16.01 8
መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል? በተባለው መጽሐፍ ማስጠናት መጀመር ያለብህ መቼ ነው?—km 3/13 9 አን. 10
መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምረናል?
ክለሳዎቹንና ተጨማሪ ሐሳቦቹን ልትጠቀምባቸው የሚገባው እንዴት ነው?—mwb16.11 5 አን. 2-3
በዛሬው ጊዜ የይሖዋን ፈቃድ የሚያደርጉት እነማን ናቸው?
ከመጽሐፍ ቅዱስ ጥናትህ ጋር በዚህ ብሮሹር ላይ መወያየት ያለብህ መቼ ነው?—mwb17.03 8 አን. 1
በዚህ ብሮሹር ተጠቅሞ ውይይት ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?—mwb17.03 8 ሣጥን