ክርስቲያናዊ ሕይወት
ከኦሪጅናል መዝሙሮቻችን ምን ትምህርት እናገኛለን?
ከኦሪጅናል መዝሙሮቻችን መካከል በጣም የምትወዱት የትኛውን ነው? ለምንስ? ቪዲዮዎቹ በዕለት ተዕለት ሕይወታችን የሚያጋጥሙንን ነገሮች እንደሚያሳዩ ይሰማችኋል? ኦሪጅናል መዝሙሮች ይዘታቸውም ሆነ ዓይነታቸው የተለያየ ስለሆነ እያንዳንዱ ሰው የሚወደውን ሙዚቃ ለማግኘት አይቸገርም። ሆኖም መዝሙሮቹም ሆኑ ቪዲዮዎቻቸው ከመዝናኛ ያለፈ ጠቀሜታ አላቸው።
እያንዳንዱ ኦሪጅናል መዝሙር በክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን ልንጠቀምበት የምንችል አስፈላጊ ትምህርት ይዟል። አንዳንዶቹ መዝሙሮች በእንግዳ ተቀባይነት፣ በአንድነት፣ በጓደኝነት፣ በድፍረት፣ በፍቅር ወይም በእምነት ላይ የሚያተኩሩ ናቸው። ሌሎቹ ደግሞ ወደ ይሖዋ ስለመመለስ፣ ይቅር ባይ ስለመሆን፣ በየዕለቱ ንጹሕ አቋምን ስለመጠበቅና መንፈሳዊ ግቦችን ስለማውጣት የሚያወሱ ናቸው። ሌላው ቀርቶ በሞባይል ስልክ አጠቃቀም ረገድ ሚዛናዊ ስለመሆን የሚናገር መዝሙር አለ። እናንተስ ከኦሪጅናል መዝሙሮች ምን ሌሎች ትምህርቶች አግኝታችኋል?
ሩቅ አይደለም ያ ጊዜ የተባለውን የኦሪጅናል መዝሙር ቪዲዮ ተመልከቱ፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክሩ፦