ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘፀአት 8–9
ኩራተኛው ፈርዖን ሳያውቀው የአምላክን ዓላማ አስፈጸመ
የግብፅ ፈርዖኖች ራሳቸውን እንደ አማልክት ይቆጥሩ ነበር። ይህን ማወቃችን ፈርዖን በጣም ኩራተኛ የነበረው እንዲሁም ሙሴንና አሮንን አልፎ ተርፎም የራሱን አስማተኛ ካህናት እንኳ ለመስማት ፈቃደኛ ያልሆነው ለምን እንደሆነ ለመገንዘብ ይረዳናል።
ሌሎች ሰዎች የሚሰጡህን ሐሳብ ታዳምጣለህ? አንድ ሰው ምክር ቢሰጥህ በአመስጋኝነት ትቀበላለህ? ወይስ ሁልጊዜ ትክክል እንደሆንክ ይሰማሃል? “ኩራት ጥፋትን . . . ይቀድማል።” (ምሳሌ 16:18) ከኩራት መራቃችን ምንኛ አስፈላጊ ነው!