ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ዘፀአት 21–22
ይሖዋ ለሕይወት ያለውን አመለካከት አንጸባርቁ
ሕይወት በይሖዋ ዘንድ ውድ ነው። እኛስ እንዲህ ዓይነት አመለካከት እንዳለን ማሳየት የምንችለው እንዴት ነው?
ለአገልግሎት ያለህን ቅንዓት በማቀጣጠል እንዲህ ያለውን ፍቅር አሳይ።—1ቆሮ 9:22, 23፤ 2ጴጥ 3:9
ምንጊዜም ለደህንነት ትልቅ ቦታ እንደምትሰጥ አሳይ።—ምሳሌ 22:3
ለሕይወት አክብሮት ማሳየት ከደም ዕዳ ነፃ ከመሆን ጋር የሚያያዘው እንዴት ነው?