ክርስቲያናዊ ሕይወት
ጊዜያችሁንና ጉልበታችሁን መስጠት ትችላላችሁ?
ኢሳይያስ በትንቢት እንደተናገረው የይሖዋ ድርጅት ምድራዊ ክፍል ታይቶ በማይታወቅ መጠን እድገት እያደረገ ነው። (ኢሳ 54:2) በዚህም ምክንያት አዳዲስ የጉባኤና የትላልቅ ስብሰባ አዳራሾችን እንዲሁም የቅርንጫፍ ቢሮ ሕንፃዎችን መገንባት አስፈላጊ ሆኗል። እነዚህ ሕንፃዎች ከተገነቡ በኋላ እንክብካቤ ያስፈልጋቸዋል፤ አንዳንዶቹ ደግሞ ከጊዜ በኋላ መታደስ ሊያስፈልጋቸው ይችላል። ይህ ሁኔታ ለይሖዋ ጊዜያችንንና ጉልበታችንን ለመስጠት የሚያስችል አጋጣሚ የሚፈጥርልን እንዴት ነው?
የአገልግሎት ቡድናችን የስብሰባ አዳራሹን የሚያጸዳበት ተራ ሲደርስ በሥራው መካፈል እንችላለን
የስብሰባ አዳራሹን ለመጠገን በሚሰጠው ሥልጠና ላይ መካፈል እንችላለን
የአካባቢ ንድፍ/ግንባታ ፈቃደኛ ሠራተኞች ማመልከቻ (DC-50) በመሙላት በአቅራቢያችን በሚካሄዱ የግንባታና የጥገና ፕሮጀክቶች ላይ በየተወሰነ ጊዜው መካፈል እንችላለን
የፈቃደኛ ሠራተኞች ፕሮግራም ማመልከቻ (A-19) በመሙላት በቅርንጫፍ ቢሯችን ክልል ውስጥ በቤቴል ወይም በሌላ የቅርንጫፍ ቢሮው ሕንፃ ለአንድ ሳምንት ወይም ከዚያ ለሚበልጥ ጊዜ እገዛ ማበርከት እንችላለን
አዲስ የግንባታ ፕሮጀክት ታቅዷል—ተቀንጭቦ የተወሰደ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
የምንጠቀምባቸው ቪዲዮዎች ቁጥር ከ2014 አንስቶ ምን ዓይነት አስደናቂ ጭማሪ አሳይቷል?
እያደገ የመጣውን የቪዲዮ ሥራ ለማስተናገድ የትኛው ፕሮጀክት ታቅዷል? ግንባታው የሚካሄደው ከመቼ እስከ መቼ ነው?
ፈቃደኛ ሠራተኞች በዚህ ሥራ መካፈል የሚችሉት እንዴት ነው?
በራማፖ በሚካሄደው ግንባታ መካፈል የሚፈልጉ ሰዎች ማመልከቻ (DC-50) በመሙላት በአቅራቢያቸው በሚካሄዱ የአካባቢ ንድፍና ግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ መካፈል ያለባቸው ለምንድን ነው?
ይሖዋ ይህን ፕሮጀክት እየመራው እንዳለ የሚያሳይ ምን ማስረጃ አለ?
በግንባታ ሥራው በቀጥታ መካፈል ባንችልም እንኳ ይህን ፕሮጀክት መደገፍ የምንችለው እንዴት ነው?