ክርስቲያናዊ ሕይወት | ለአዲሱ የአገልግሎት ዓመት ግብ አውጡ
በቲኦክራሲያዊ የግንባታ ሥራዎች መካፈል
በቲኦክራሲያዊ የግንባታ ሥራዎች መካፈል የቅዱስ አገልግሎት ክፍል ነው። (ዘፀ 36:1) የአካባቢ ንድፍ/ግንባታ ፈቃደኛ ሠራተኞች ማመልከቻ (DC-50) በመሙላት በአቅራቢያህ በሚካሄዱ የግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ አልፎ አልፎ መካፈል ትችል ይሆን? ወይም ደግሞ የፈቃደኛ ሠራተኞች ፕሮግራም ማመልከቻ (A-19) በመሙላት ራቅ ብለው በሚገኙ ፕሮጀክቶች ላይ ለተወሰኑ ሳምንታት ወይም ወራት ለመካፈል ራስህን ማቅረብ ትችል ይሆን? በግንባታ ፕሮጀክቶች ላይ በፈቃደኝነት ለመካፈል የግንባታ ሥራ ልምድ አያስፈልግም።—ነህ 2:1, 4, 5
ወደተከፈተላችሁ የሥራ በር በእምነት ግቡ—በቲኦክራሲያዊ የግንባታ ሥራዎች መካፈል የሚለውን አጭር ድራማ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተለውን ጥያቄ ለመመለስ ሞክር፦
ሳራ ምን አስጨንቋት ነበር? የረዳትስ ምንድን ነው?