ክርስቲያናዊ ሕይወት
በኅዳር ወር የአምላክን መንግሥት ለማስተዋወቅ የሚደረግ ልዩ ዘመቻ
ኢየሱስ “የአምላክን መንግሥት ምሥራች” አውጇል። (ሉቃስ 4:43) እንዲሁም ሰዎች ይህ መንግሥት እንዲመጣ እንዲጸልዩ አስተምሯል። (ማቴ 6:9, 10) በኅዳር ወር የአምላክን መንግሥት ለማስተዋወቅ ልዩ ጥረት እናደርጋለን። (ማቴ 24:14) በዘመቻው ሙሉ ተሳትፎ ለማድረግ ፕሮግራማችሁን አስተካክሉ። በዚህ ወር ረዳት አቅኚ የሚሆኑ አስፋፊዎች ለ30 ሰዓት ወይም ለ50 ሰዓት ማገልገል ይችላሉ።
በክልላችሁ ውስጥ በተቻለ መጠን ለብዙ ሰው ስለ አምላክ መንግሥት የሚናገር ጥቅስ ለማንበብ ጥረት አድርጉ። ጥቅስ ስትመርጡ የምታነጋግሩትን ሰው ሃይማኖት ግምት ውስጥ አስገቡ። የምትመሠክሩላቸው ሰዎች ፍላጎት ካሳዩ ለሕዝብ የሚሰራጨውን መጠበቂያ ግንብ ቁጥር 2 2020 አበርክቱላቸው። ከዚያም በአጭር ጊዜ ውስጥ ተመልሳችሁ አነጋግሯቸው፤ እንዲሁም በማስተማሪያ መሣሪያዎቻችን ውስጥ የሚገኝ ጽሑፍ ተጠቅማችሁ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ለማስጀመር ጥረት አድርጉ። የአምላክ መንግሥት ሰብዓዊ መንግሥታትን በሙሉ የሚያደቅበት ጊዜ በጣም ቀርቧል። (ዳን 2:44፤ 1ቆሮ 15:24, 25) እንግዲያው ሁላችንም ለይሖዋና ለመንግሥቱ ያለንን ታማኝነት ማሳየት የምንችልበትን ይህን ልዩ አጋጣሚ በተሟላ መንገድ እንጠቀምበት!
የአምላክ መንግሥት ምድርን ገነት ያደርጋል!