የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb21 ግንቦት ገጽ 11
  • በግለት ማስተማር

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በግለት ማስተማር
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በጋለ ስሜት መናገር
    በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ከሚሰጠው ሥልጠና ተጠቀም
  • በጋለ ስሜት መናገር
    ለማንበብ እና ለማስተማር የተቻለህን ሁሉ ጥረት አድርግ
  • ጥያቄዎችን ተጠቀሙ
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
  • የሰዎችን ልብ መንካት
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
mwb21 ግንቦት ገጽ 11
አንድ ወንድም አንድን በዕድሜ የገፋ ሰው መጽሐፍ ቅዱስ ሲያስጠና፤ ፊቱ ላይ ፈገግታ የሚነበብበት ከመሆኑም ሌላ በእጁ አካላዊ መግለጫዎች እየተጠቀመ ነው።

በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር | በአገልግሎት የምታገኙትን ደስታ አሳድጉ

በግለት ማስተማር

ግለት የሚጋባ ነገር ነው። የምናነጋግራቸው ሰዎች በትኩረት እንዲያዳምጡን ሊያደርግ ይችላል። ለምንናገረው መልእክት ምን ያህል ክብደት እንደምንሰጥም ያሳያል። ያደግንበት ባሕል ወይም ባሕርያችን ምንም ይሁን ምን በግለት የማስተማር ችሎታን ማዳበር እንችላለን። (ሮም 12:11) እንዴት?

አንደኛ፣ የምትናገረው መልእክት ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አስብ። “የተሻለ ነገር እንደሚመጣ ምሥራች” የማብሰር መብት አግኝተሃል። (ሮም 10:15) ሁለተኛ፣ ምሥራቹ በሰዎች ሕይወት ላይ ምን ያህል ለውጥ እንደሚያመጣ አሰላስል። ሰዎች፣ የምንናገረው መልእክት በጣም ያስፈልጋቸዋል። (ሮም 10:13, 14) በመጨረሻም ሞቅ ባለ ስሜት ተናገር፤ ተስማሚ የሆኑ አካላዊ መግለጫዎችን ተጠቀም፤ ፊትህ ላይ የሚነበበው ነገርም የውስጥህን ስሜት የሚገልጽ ሊሆን ይገባል።

ደቀ መዛሙርት የማድረጉ ሥራ የሚያስገኘውን ደስታ አጣጥሙ—ክህሎታችሁን አሻሽሉ—በግለት ማስተማር የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ‘ደቀ መዛሙርት የማድረጉ ሥራ የሚያስገኘውን ደስታ አጣጥሙ—ክህሎታችሁን አሻሽሉ—በግለት ማስተማር’ ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ምስል። ኒታ፣ ጄድ የጥናት ፕሮግራማቸውን ሰርዛባታለች፤ በመሆኑም ኒታ ፊቷ ላይ የተስፋ መቁረጥ ስሜት ይነበባል።

    ኒታ፣ ጄድን ስታስጠና ግለቷ እንዲቀዘቅዝ ያደረገው ምንድን ነው?

  • ‘ደቀ መዛሙርት የማድረጉ ሥራ የሚያስገኘውን ደስታ አጣጥሙ—ክህሎታችሁን አሻሽሉ—በግለት ማስተማር’ ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ምስል። መጽሐፍ ቅዱስ በሚያጠኑበት ወቅት ጄድ እንደተሰላቸች ያስታውቃል።

    ኒታ ቅንዓቷን መልሳ ለማቀጣጠል የረዳት ምንድን ነው?

  • ‘ደቀ መዛሙርት የማድረጉ ሥራ የሚያስገኘውን ደስታ አጣጥሙ—ክህሎታችሁን አሻሽሉ—በግለት ማስተማር’ ከተባለው ቪዲዮ የተወሰደ ምስል። ጄድ እና ኒታ ጥናታቸውን ከጨረሱ በኋላ በደስታና ሞቅ ባለ ስሜት ሲጨዋወቱ።

    ግለት የሚጋባ ነገር ነው

    በምናነጋግራቸው ሰዎች አዎንታዊ ጎን ላይ ማተኮር ያለብን ለምንድን ነው?

  • የእኛ ግለት በጥናቶቻችንም ሆነ በሌሎች ላይ ምን ውጤት ሊኖረው ይችላል?

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ