በአገልግሎት ውጤታማ ለመሆን ተጣጣር | በአገልግሎት የምታገኙትን ደስታ አሳድጉ
አብረውን የሚያገለግሉ ክርስቲያኖች የሚሰጡንን እርዳታ መቀበል
ይሖዋ እኛን ለመርዳት ‘መላውን የወንድማማች ማኅበር’ ሰጥቶናል። (1ጴጥ 5:9) ወንድሞቻችንና እህቶቻችን፣ በአገልግሎት ላይ የሚያጋጥሙንን ተፈታታኝ ሁኔታዎች በተሳካ ሁኔታ እንድንወጣ ይረዱናል። ለምሳሌ ያህል ጳውሎስ፣ እንደ አቂላና ጵርስቅላ፣ ሲላስ እንዲሁም ጢሞቴዎስ ያሉ ክርስቲያኖች ካደረጉለት እገዛ ተጠቅሟል።—ሥራ 18:1-5
አብረውን የሚያገለግሉት ክርስቲያኖች በአገልግሎት ረገድ ሊረዱን የሚችሉት እንዴት ነው? ለተቃውሞ ሐሳብ እንዴት መልስ እንደምንሰጥ፣ ተመላልሶ መጠየቅ እንዴት እንደምናደርግ፣ ጥናት እንዴት እንደምናስጀምርና እንዴት እንደምንመራ ጠቃሚ ሐሳቦች ሊያካፍሉን ይችላሉ። ጉባኤያችሁ ውስጥ፣ የሚያስፈልጋችሁን እርዳታ ሊሰጣችሁ የሚችለው ማን እንደሆነ ለማሰብ ሞክሩ፤ ከዚያም ግለሰቡን እንዲረዳችሁ ጠይቁት። ይህ ለሁለታችሁም ጠቃሚ እንደሚሆን ጥርጥር የለውም፤ እንዲሁም አንዳችሁ ለሌላው የደስታ ምንጭ እንድትሆኑ ያስችላችኋል።—ፊልጵ 1:25
ደቀ መዛሙርት የማድረጉ ሥራ የሚያስገኘውን ደስታ አጣጥሙ—የይሖዋን እርዳታ ተቀበሉ—ወንድሞቻችን የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
ኒታ፣ ጄድ በስብሰባዎች ላይ እንድትገኝ ለማበረታታት የሞከረችው እንዴት ነው?
ጥናት ስንመራ ሌሎች አስፋፊዎችን መጋበዛችን ጠቃሚ የሆነው ለምንድን ነው?
አንድን ሰው ደቀ መዝሙር የሚያደርገው መላው ጉባኤ ነው
ጄድ እና አቢጌል ምን ተመሳሳይ ፍላጎት አላቸው?
አብረዋችሁ ከሚያገለግሉት ክርስቲያኖች፣ የትኞቹን ለአገልግሎት የሚጠቅሙ ክህሎቶች መማር ትችላላችሁ?