የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb22 መጋቢት ገጽ 13
  • ሁሉም ፈተናዎች የሚያበቁበት ጊዜ አላቸው

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ሁሉም ፈተናዎች የሚያበቁበት ጊዜ አላቸው
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2022
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ይሖዋ ፈተናዎችን እንድንወጣ ይረዳናል
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
  • ትዕግሥት ማሳየታችሁን ቀጥሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2023
  • በትዕግሥት ለመጠበቅ ፈቃደኛ ናችሁ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2017
  • ይሖዋን በትዕግሥት ጠብቁ
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2022
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2022
mwb22 መጋቢት ገጽ 13
“በተከፋፈለ ዓለም ውስጥ አንድነት ያለው ሕዝብ” ከሚለው ቪዲዮ ላይ የተወሰደ ምስል፦ 1. ጥቁር ወንድሞችና እህቶች ብቻ የተገኙበት ትልቅ ስብሰባ። 2. ጥቁርና ነጭ የቆዳ ቀለም ያላቸው ሽማግሌዎችና ሚስቶቻቸው አንድ ላይ ፎቶ ሲነሱ። 3. የተለያየ ዕድሜና የቆዳ ቀለም ያላቸው ሁለት እህቶች በአደባባይ ምሥክርነት ሲካፈሉ።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ሁሉም ፈተናዎች የሚያበቁበት ጊዜ አላቸው

የሚያጋጥሙን ፈታኝ ሁኔታዎች በቀላሉ ተስፋ ሊያስቆርጡን ይችላሉ፤ በተለይ ለረጅም ጊዜ ሲቀጥሉ ሁኔታው ይበልጥ ከባድ ይሆንብናል። ዳዊት፣ ንጉሥ ሳኦል የሚያደርስበት መከራ አንድ ቀን እንደሚያበቃና ይሖዋ ቃል በገባው መሠረት ንጉሥ እንደሚሆን ያውቅ ነበር። (1ሳሙ 16:13) ዳዊት እምነት የነበረው መሆኑ በትዕግሥት ይሖዋን እንዲጠባበቅ ረድቶታል።

ችግር ሲያጋጥመን ብልሃት፣ እውቀት ወይም የማመዛዘን ችሎታ ተጠቅመን ችግሩን መፍታት እንችል ይሆናል። (1ሳሙ 21:12-14፤ ምሳሌ 1:4) አንዳንድ ችግሮች ግን ከመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶች ጋር በሚስማማ መልኩ አቅማችን የፈቀደውን ሁሉ ብናደርግም ላይቀረፉ ይችላሉ። እንዲህ ያሉ ሁኔታዎች ሲያጋጥሙን በትዕግሥት ይሖዋን ልንጠባበቅ ይገባል። በቅርቡ ይሖዋ፣ ያጋጠሙንን መከራዎች በሙሉ በማስወገድ ‘እንባን ሁሉ ከዓይናችን ያብሳል።’ (ራእይ 21:4) ከችግራችን እፎይታ የምናገኘው ይሖዋ ጣልቃ ገብቶ ስላስወገደልንም ሆነ በሌሎች ምክንያቶች፣ ስለ አንድ ነገር እርግጠኞች ነን፦ ሁሉም ፈተናዎች የሚያበቁበት ጊዜ አላቸው። ይህን ማወቃችን በተወሰነ መጠንም ቢሆን ያጽናናናል።

በተከፋፈለ ዓለም ውስጥ አንድነት ያለው ሕዝብ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • በደቡባዊ ዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩ አንዳንድ ክርስቲያኖች ምን ተፈታታኝ ሁኔታዎች አጋጥመዋቸው ነበር?

  • ትዕግሥትና ፍቅር እንዳላቸው ያሳዩት እንዴት ነው?

  • “ይበልጥ አስፈላጊ [በሆኑት] ነገሮች” ላይ ትኩረት ማድረጋቸውን የቀጠሉት እንዴት ነው?—ፊልጵ 1:10

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ