የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb22 ሐምሌ ገጽ 5
  • አስፋፊዎች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉበት ቦታ መዛወር

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አስፋፊዎች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉበት ቦታ መዛወር
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2022
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በቅርንጫፍ ቢሮ ውስጥ ምን ዓይነት ሥራ ይከናወናል?
    በዛሬው ጊዜ የይሖዋን ፈቃድ የሚያደርጉት እነማን ናቸው?
  • አገልግሎትህን ማስፋት የምትችልባቸው መንገዶች
    የይሖዋን ፈቃድ ለማድረግ የተደራጀ ሕዝብ
  • ‘ወደ መቄዶንያ መሻገር’ ትችላለህ?
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2011
  • “መሄድ ይኖርብኝ ይሆን?”
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2000
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2022
mwb22 ሐምሌ ገጽ 5
“ወደተከፈተላችሁ የሥራ በር በእምነት ግቡ—አስፋፊዎች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉበት ቦታ መዛወር” በሚለው ቪዲዮ ላይ የተመሠረቱ ሥዕላዊ መግለጫዎች። ምስሎች፦ 1. ገብርኤል ምርምር ሲያደርግ። 2. ቅርንጫፍ ቢሮውን ስለማነጋገር አንድን ሽማግሌ ሲያማክር። 3. በልዩ የስብከት ዘመቻ ወቅት ከጓደኛው ከሳሙኤል ጋር ሲያገለግል።

ክርስቲያናዊ ሕይወት | ለአዲሱ የአገልግሎት ዓመት ግብ አውጡ

አስፋፊዎች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉበት ቦታ መዛወር

አገልግሎትን ለማስፋት ሲባል የለመዱትን አካባቢ ትቶ ወደ ሌላ ቦታ መዛወር እምነት ይጠይቃል። (ዕብ 11:8-10) አስፋፊዎች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉበት ቦታ ለመዛወር የምታስቡ ከሆነ የጉባኤ ሽማግሌዎቻችሁን አነጋግሩ። ወጪያችሁን ለማስላትና ቦታ ለመምረጥ ምን እርምጃ ልትወስዱ ትችላላችሁ? ሰባኪዎች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉበት ቦታ ስለመዛወር በጽሑፎቻችን ላይ የወጡ ሐሳቦችን አንብቡ። ወደ ሌላ ጉባኤ ተዛውረው ማገልገል የቻሉ ወንድሞችንና እህቶችን አማክሩ። (ምሳሌ 15:22) በጸሎት የይሖዋን አመራር ጠይቁ። (ያዕ 1:5) ልትሄዱበት ስላሰባችሁት ቦታ ምርምር አድርጉ። የሚቻል ከሆነ ደግሞ ውሳኔ ከማድረጋችሁ በፊት ሰፋ ያለ ጊዜ ወስዳችሁ አካባቢውን ጎብኙ።

ወደተከፈተላችሁ የሥራ በር በእምነት ግቡ—አስፋፊዎች ይበልጥ ወደሚያስፈልጉበት ቦታ መዛወር የሚለውን አጭር ድራማ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተለውን ጥያቄ ለመመለስ ሞክር፦

  • ገብርኤል ምን ተፈታታኝ ሁኔታ አጋጥሞታል? የረዳውስ ምንድን ነው?

በአቅራቢያችሁ ስለሚገኙ እርዳታ የሚያስፈልጋቸው ጉባኤዎች መረጃ ማግኘት ከፈለጋችሁ የወረዳ የበላይ ተመልካቻችሁን አማክሩ። ራቅ ስላሉ ጉባኤዎች መረጃ ማግኘት ከፈለጋችሁ ደግሞ በጉባኤያችሁ የአገልግሎት ኮሚቴ በኩል ወደ ቅርንጫፍ ቢሮው ደብዳቤ ጻፉ። ጉባኤዎቹ የሚገኙት ከቅርንጫፍ ቢሯችሁ ክልል ውጭ ከሆነ የዚያን አገር ሥራ በበላይነት ወደሚከታተለው ቅርንጫፍ ቢሮ ጻፉ። ማገልገል የምትፈልጉበት አካባቢ ካለ ደብዳቤያችሁ ላይ ለይታችሁ መጥቀስ ትችላላችሁ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ