ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
የትዳር ጓደኛችሁን በጥበብ ምረጡ
ሰለሞን ጣዖት አምላኪ ሴቶችን በማግባት የሞኝነት ድርጊት ፈጽሟል (1ነገ 11:1, 2፤ w18.07 18 አን. 7)
ሚስቶቹ ቀስ በቀስ ልቡ ከይሖዋ እንዲርቅ አድርገዋል (1ነገ 11:3-6፤ w19.01 15 አን. 6)
ይሖዋ በሰለሞን ላይ ተቆጣ (1ነገ 11:9, 10፤ w18.07 19 አን. 9)
ክርስቲያኖች “በጌታ ብቻ” እንዲያገቡ የአምላክ ቃል ይመክራል። (1ቆሮ 7:39) ሆኖም አንድ ሰው ስለተጠመቀ ብቻ ጥሩ የትዳር ጓደኛ ይሆናል ማለት አይደለም። ዋናው ጥያቄ ይህ ነው፦ ‘ግለሰቡ ይሖዋን በሙሉ ነፍስ እንዳገለግል ሊረዳኝ ይችላል? ለይሖዋ ያለው ጥልቅ ፍቅር በጊዜ ተፈትኗል?’ አንድን ሰው ለማግባት ከመወሰናችሁ በፊት ጊዜ ወስዳችሁ ግለሰቡን በደንብ ለማወቅ ጥረት አድርጉ።