ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት
ማጽናኛ ለማግኘት ወደ ይሖዋ ዘወር በሉ
ኤልያስ ስለፈራ ሕይወቱን ለማትረፍ ሸሽቷል (1ነገ 19:3, 4፤ w19.06 15 አን. 5)
ይሖዋ የሚያስፈልገውን ድጋፍ አድርጎለታል እንዲሁም ኃይሉን አስደናቂ በሆነ መንገድ አሳይቶታል (1ነገ 19:5-7, 11, 12፤ ia 103 አን. 13፤ 106 አን. 21)
ይሖዋ ሥራ ሰጥቶታል (1ነገ 19:15-18፤ ia 106 አን. 22)
ይሖዋ ዛሬ እኛን የሚያነጋግረን በቃሉ በኩል ነው፤ ከልቡ እንደሚያስብልንና በእሱ አገልግሎት ውስጥ የምናከናውነው ሥራ ትርጉም ያለው እንደሆነ በቃሉ አማካኝነት ያስታውሰናል።—1ቆሮ 15:58፤ ቆላ 3:23