የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb23 ጥር ገጽ 11
  • የአምላክን አስተሳሰብ ለማወቅ ጥረት አድርጉ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአምላክን አስተሳሰብ ለማወቅ ጥረት አድርጉ
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በይሖዋ እንደምንታመን የሚያሳዩ ውሳኔዎች
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
  • ይሖዋን የሚያስደስቱ ውሳኔዎችን አድርግ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2025
  • መጽሐፍ ቅዱስን በየዕለቱ ማንበብ ጥበብ ለማግኘት ይረዳል
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
  • ወላጆች—ልጆቻችሁ ይሖዋን ማስደሰት የሚችሉት እንዴት እንደሆነ አስተምሯቸው
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
mwb23 ጥር ገጽ 11
“‘በጽናት ሩጡ’—ገንቢ ምግብ ተመገቡ” በሚለው ቪዲዮ ላይ የተመሠረተ ሥዕል። ሬቤካ “የሕይወት አመጣጥ—መልስ የሚያሻቸው አምስት ጥያቄዎች” የተባለውን ብሮሹር ተጠቅማ ምርምር ስታደርግ።

ክርስቲያናዊ ሕይወት

የአምላክን አስተሳሰብ ለማወቅ ጥረት አድርጉ

በምናደርገው ነገር ሁሉ ይሖዋን ማስደሰት እንፈልጋለን። (ምሳሌ 27:11) ይህንንም ለማድረግ፣ በግልጽ የተቀመጠ መመሪያ ወይም ትእዛዝ በማይኖርበት ጊዜም እንኳ የይሖዋን አስተሳሰብ የሚያንጸባርቅ ውሳኔ ማድረግ ይጠበቅብናል። ታዲያ ይህን ለማድረግ ምን ይረዳናል?

ቋሚ የሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ፕሮግራም ይኑራችሁ። መጽሐፍ ቅዱስን ባነበብን ቁጥር ከይሖዋ ጋር ጊዜ እያሳለፍን እንዳለ ሊቆጠር ይችላል። ይሖዋ ሕዝቡን የያዘበትን መንገድ በማጥናት እንዲሁም በእሱ ዓይን ጥሩ ወይም መጥፎ ያደረጉ ሰዎችን ታሪክ በመመርመር ስለ ይሖዋ አስተሳሰብ መማር እንችላለን። ውሳኔ ማድረግ የሚጠይቅ ሁኔታ ሲያጋጥመን መንፈስ ቅዱስ ከአምላክ ቃል የተማርናቸውን ጠቃሚ ትምህርቶችና መሠረታዊ ሥርዓቶች እንድናስታውስ ይረዳናል።—ዮሐ 14:26

ምርምር አድርግ። ውሳኔ ማድረግ ሲያስፈልጋችሁ ራሳችሁን እንዲህ ብላችሁ ጠይቁ፦ ‘ስለ ጉዳዩ ይሖዋ ያለውን አመለካከት ለማወቅ የሚረዱኝ የትኞቹ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅሶች ወይም ዘገባዎች ናቸው?’ ይሖዋ እንዲረዳችሁ ጸልዩ፤ እንዲሁም ለእናንተ ሁኔታ የሚሠሩ የመጽሐፍ ቅዱስ መሠረታዊ ሥርዓቶችን ለማግኘትና በሥራ ላይ ለማዋል እንድትችሉ በቋንቋችሁ የተዘጋጁ የምርምር መሣሪያዎችን ተጠቀሙ።—መዝ 25:4

‘በጽናት ሩጡ’—ገንቢ ምግብ ተመገቡ የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • በቪዲዮው ላይ የታየችው ወጣት እህት ምን ዓይነት ተጽዕኖ መቋቋም አስፈልጓታል?

  • እናንተስ እንዲህ ዓይነት ተጽዕኖዎችን ለመቋቋም የምርምር መሣሪያዎችን መጠቀም የምትችሉት እንዴት ነው?

  • ጊዜ ወስደን ምርምርና የግል ጥናት ማድረጋችን የሚጠቅመን እንዴት ነው?—ዕብ 5:13, 14

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ