የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb23 ግንቦት ገጽ 5
  • ለኢኮኖሚ ቀውስ ተዘጋጅታችኋል?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ለኢኮኖሚ ቀውስ ተዘጋጅታችኋል?
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ዝግጁ ናችሁ?
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2020
  • “በመጨረሻዎቹ ቀናት” መጨረሻ ለሚያጋጥሙ ነገሮች ዝግጁ ሁኑ
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2021
  • በይሖዋ እንደምንታመን የሚያሳዩ ውሳኔዎች
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
  • ሕዝባዊ ዓመፅ ቢያጋጥም ዝግጁ ናችሁ?
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2022
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
mwb23 ግንቦት ገጽ 5

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ለኢኮኖሚ ቀውስ ተዘጋጅታችኋል?

በዓለም ዙሪያ የኢኮኖሚ አለመረጋጋት ቢከሰት አንደናገጥም። ለምን? ምክንያቱም የምንኖረው በመጨረሻዎቹ ቀናት መጨረሻ እንደሆነ እናውቃለን፤ መጽሐፍ ቅዱስም ተስፋችንን “አስተማማኝነት በሌለው ሀብት” ላይ እንዳንጥል ይመክረናል። (1ጢሞ 6:17፤ 2ጢሞ 3:1) ለኢኮኖሚ ቀውስ መዘጋጀት የምንችልበትን መንገድ በተመለከተ ከኢዮሳፍጥ ምሳሌ ምን እንማራለን?

የጠላት ሠራዊት ይሁዳን ለመውረር በመጣበት ወቅት ኢዮሳፍጥ በይሖዋ ታምኗል። (2ዜና 20:9-12) በተጨማሪም ምሽጎችን በመገንባትና የጦር ሰፈሮችን በማቋቋም ብሔሩን ለሚሰነዘርባቸው ጥቃት ለማዘጋጀት ተግባራዊ እርምጃ ወስዷል። (2ዜና 17:1, 2, 12, 13) እኛም የሚያጋጥመንን አስቸጋሪ ሁኔታ ለመቋቋም እንደ ኢዮሳፍጥ በይሖዋ መታመንና ተግባራዊ እርምጃ መውሰድ ይኖርብናል።

ለኢኮኖሚ ቀውስ ለመዘጋጀት ምን ማድረግ እንችላለን?

በመንፈሳዊ መዘጋጀት፦ ባላችሁ ነገር የመርካት ዝንባሌ አዳብሩ፤ እንዲሁም ይሖዋ የሚያስፈልጋችሁን ነገር የማሟላት ችሎታ እንዳለው ያላችሁን እምነት አጠናክሩ። (ማቴ 6:26፤ 1ጢሞ 6:8) የሚያስፈልጓችሁን ነገሮች ለማሟላት ስትሉ የመጽሐፍ ቅዱስን መሠረታዊ ሥርዓቶች ላለመጣስ ቁርጥ ውሳኔ አድርጉ። (ሮም 2:21) ኤሌክትሪክ ወይም ኢንተርኔት ቢቋረጥ መንፈሳዊ ምግብ እንዴት ማግኘት እንደምትችሉ አስቡ። የተወሰኑ የታተሙ ጽሑፎች እንዲኖሯችሁ አድርጉ፤ እንዲሁም ከተቻለ የጽሑፎችን ኤሌክትሮኒክ ቅጂ ቀደም ብላችሁ አውርዱ።

በቁሳዊ መዘጋጀት፦ የኢኮኖሚ ችግር ከመከሰቱ በፊት ዕዳና አላስፈላጊ ወጪዎችን ቀንሱ። (ምሳሌ 22:7) የሚቻል ከሆነ፣ ምግብና ሌሎች አስፈላጊ ቁሳቁሶችን በሚያስፈልጋችሁ መጠን አከማቹ። አንዳንዶች ገንዘብ ለመቆጠብ ሲሉ የጓሮ አትክልቶችን ለመትከል ይወስኑ ይሆናል።

አደጋ ቢያጋጥም ዝግጁ ናችሁ? የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

“አደጋ ቢያጋጥም ዝግጁ ናችሁ?” ከሚለው ቪዲዮ የተወሰደ ፎቶግራፍ። መጽሐፍ ቅዱስ፣ የአደጋ ጊዜ ቦርሳና ስልክ እንዲሁም የግንባታ ሠራተኞች ይታያሉ።
  • ለአደጋ ለመዘጋጀት በግለሰብ ደረጃ ምን ማድረግ እንችላለን?

“አደጋ ቢያጋጥም ዝግጁ ናችሁ?” ከሚለው ቪዲዮ የተወሰደ ፎቶግራፍ። ወንድሞች በመገንባትና ከጭነት መኪና ላይ ቁሳቁሶችን በማውረድ በእርዳታ ሥራ ሲካፈሉ።
  • ሌሎችን ለመርዳት መዘጋጀት የምንችለው እንዴት ነው?

ግብ

በቤተሰብ አምልኳችሁ ወቅት ንቁ! ቁጥር 1 2022⁠ን ከልሱ። ለአደጋ ለመዘጋጀት ልትወስዱ የምትችሏቸውን ተጨማሪ እርምጃዎች ተወያዩ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ