የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb23 ሐምሌ ገጽ 3
  • ‘ለምሥራቹ መሟገትና በሕግ የጸና እንዲሆን ማድረግ’

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ‘ለምሥራቹ መሟገትና በሕግ የጸና እንዲሆን ማድረግ’
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ምሥራቹ ሕጋዊ ከለላ እንዲያገኝ ማድረግ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
  • በይሖዋ እንደምንታመን የሚያሳዩ ውሳኔዎች
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
  • የጥያቄ ሣጥን
    የመንግሥት አገልግሎታችን—2009
  • የማታውቋቸው ነገሮች እንዳሉ አምናችሁ በመቀበል ልካችሁን እንደምታውቁ አሳዩ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2025
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
mwb23 ሐምሌ ገጽ 3
ፎቶግራፎች፦ 1. ጋቲ እና ማሪ ባርኔት። 2. ወንድም ኮኪናኪስና ሌሎች በአውሮፓ የሰብዓዊ መብቶች ፍርድ ቤት ውስጥ። 3. የይሖዋ ምሥክሮች ሩሲያ ውስጥ ባለው የሮስቶቭ ክልላዊ ፍርድ ቤት ውስጥ። 4. የተወሰኑ ወንድሞች ከደቡብ ኮሪያ የሕገ መንግሥት ፍርድ ቤት ውጭ ቆመው።

ከሳሽ ኮኪናኪስ፣ ተከሳሽ ግሪክ፦ Droit réservé

ከላይ በስተ ግራ፦ ከሳሽ የዌስት ቨርጂኒያ የትምህርት ቦርድ፣ ተከሳሽ ባርኔት፤ ከላይ በስተ ቀኝ፦ ከሳሽ ኮኪናኪስ፣ ተከሳሽ ግሪክ፤ ከታች በስተ ግራ፦ ከሳሽ ቻ እና ሌሎች፣ ተከሳሽ ደቡብ ኮሪያ፤ ከታች በስተ ቀኝ፦ ከሳሽ የታጋንሮግ ቢሮ እና ሌሎች፣ ተከሳሽ ሩሲያ

ክርስቲያናዊ ሕይወት

‘ለምሥራቹ መሟገትና በሕግ የጸና እንዲሆን ማድረግ’

እስራኤላውያን ቤተ መቅደሱን መልሰው እንዳይገነቡ ተቃዋሚዎች ጥረት ባደረጉበት ወቅት አይሁዳውያኑ ሥራውን ለማስቀጠል የሚያስችል ሕጋዊ ፈቃድ ለማግኘት ጥረት አድርገዋል። (ዕዝራ 5:11-16) ክርስቲያኖችም በተመሳሳይ ለምሥራቹ ለመሟገትና በሕግ የጸና እንዲሆን ለማድረግ ጥረት ያደርጋሉ። (ፊልጵ 1:7) ለዚህም ሲባል በ1936 በዋናው መሥሪያ ቤት የሕግ ክፍል ተቋቁሟል። በዛሬው ጊዜ፣ በዋናው መሥሪያ ቤት ያለው የሕግ ክፍል በዓለም ዙሪያ ለመንግሥቱ ጉዳዮች ጥብቅና ይቆማል። የሕግ ክፍሉ የመንግሥቱን ጉዳዮች ያራመደውና ለአምላክ ሕዝቦች ጥቅም ያስገኘው እንዴት ነው?

በዋናው መሥሪያ ቤት ያለው የሕግ ክፍል የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • የይሖዋ ምሥክሮች ከሕግ ጋር በተያያዘ የትኞቹ ችግሮች ያጋጥሟቸዋል?

  • የትኞቹን የሕግ ድሎች አግኝተናል? ምሳሌ ስጥ

  • እያንዳንዳችን ‘ለምሥራቹ በመሟገትና በሕግ የጸና እንዲሆን በማድረግ’ ረገድ ምን ሚና መጫወት እንችላለን?

  • ከአምላክ ሕዝቦች ጋር የተያያዙ ሕግ ነክ ጉዳዮችንና በእምነታቸው ምክንያት የታሰሩ የይሖዋ ምሥክሮችን ዝርዝር ድረ ገጻችን ላይ ማግኘት የምንችለው እንዴት ነው?

በአንድ የአገልግሎት ዘርፍ ስትካፈል ባለሥልጣናት ሕግ እንደጣስክ ከነገሩህ ስለ መብትህ በመሟገት ጉዳዩን በራስህ ለመፍታት አትሞክር። ከዚህ ይልቅ፣ በትሕትናና በአክብሮት የተጠየቅከውን ነገር ወዲያውኑ አድርግ። መስበክህን እንድታቆም ያዘዘህ ፖሊስ ከሆነ ከቻልክ በዘዴ የመታወቂያውን ቁጥርና የሚሠራበትን ፖሊስ ጣቢያ ለማወቅ ጥረት አድርግ። ከዚያም ጉዳዩን ወዲያውኑ ለሽማግሌዎች አሳውቅ፤ እነሱም ተጨማሪ እገዛ ለማግኘት ቅርንጫፍ ቢሮውን ያነጋግራሉ።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ