የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • mwb23 መስከረም ገጽ 11
  • ይሖዋ መንፈሳቸው የተደቆሰባቸውን ያድናል

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ይሖዋ መንፈሳቸው የተደቆሰባቸውን ያድናል
  • ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • በጭንቀት ከመዋጥ መገላገል የምችለው እንዴት ነው?
    ንቁ!—2010
  • በይሖዋ እንደምንታመን የሚያሳዩ ውሳኔዎች
    ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
  • ይሖዋ “የተሰበረ ልብ ያላቸውን ይጠግናል”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2024
  • በከፍተኛ ሐዘን ስዋጥ ምን ማድረግ እችላለሁ?
    ወጣቶች የሚጠይቋቸው ጥያቄዎችና ተግባራዊ መሆን የሚችሉ መልሶች፣ ጥራዝ 1
ለተጨማሪ መረጃ
ክርስቲያናዊ ሕይወታችንና አገልግሎታችን​—የስብሰባው አስተዋጽኦ—2023
mwb23 መስከረም ገጽ 11

ክርስቲያናዊ ሕይወት

ይሖዋ መንፈሳቸው የተደቆሰባቸውን ያድናል

ሁሉም ሰው አልፎ አልፎ ያዝናል። የሐዘን ስሜት የመንፈሳዊ ድክመት ምልክት አይደለም። ይሖዋም እንኳ ሳይቀር ሐዘን የተሰማው ጊዜ እንዳለ ገልጿል። (ዘፍ 6:5, 6) ይሁንና በተደጋጋሚ ወይም ሁልጊዜ በሐዘን ስሜት ብንዋጥስ?

ይሖዋ እንዲረዳችሁ ጸልዩ። ይሖዋ አእምሯዊና ስሜታዊ ጤንነታችን በጣም ያሳስበዋል። ስንደሰትና ስናዝን ያስተውላል። በአስተሳሰባችንና በስሜታችን ላይ ተጽዕኖ የሚያሳድሩትን ነገሮች ይረዳል። (መዝ 7:9ለ) ከሁሉ በላይ ደግሞ፣ ይሖዋ በጣም ያስብልናል፤ እንዲሁም ሐዘንን አልፎ ተርፎም የመንፈስ ጭንቀትን ለመቋቋም ይረዳናል።—መዝ 34:18

የአእምሮ ጤንነታችሁን ተንከባከቡ። አሉታዊ ስሜቶች ደስታችንንም ሆነ አምልኳችንን ሊነኩ ይችላሉ። በዚህም የተነሳ ልባችንን ማለትም መላውን ውስጣዊ ማንነታችንን መጠበቅ ይኖርብናል።—ምሳሌ 4:23

ወንድሞቻችን ሰላማቸውን ጠብቀው እየኖሩ ያሉት እንዴት ነው?—የመንፈስ ጭንቀት ቢያጋጥማቸውም የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦

  • ኒኪ ከመንፈስ ጭንቀት ጋር የምታደርገውን ትግል ለማሸነፍ ምን ተግባራዊ እርምጃዎችን ወስዳለች?

  • ኒኪ የሕክምና እርዳታ እንደሚያስፈልጋት የተሰማት ለምንድን ነው?—ማቴ 9:12

  • ኒኪ በይሖዋ እርዳታ እንደምትታመን ያሳየችው በየትኞቹ መንገዶች ነው?

“የአእምሮ ጤንነት—መጽሐፍ ቅዱስ የሚሰጠው እርዳታ” የሚል ርዕስ ያለው ቁጥር 1 2023 “መጠበቂያ ግንብ”

ለሕዝብ የሚሰራጨውን መጠበቂያ ግንብ ቁጥር 1 2023 ቢያገኝ እንደሚጠቀም የሚሰማህ ሰው አለ?

ስሜታዊ ጤንነታችንን ለመንከባከብ ማድረግ የምንችላቸው አንዳንድ ነገሮች የትኞቹ ናቸው?

(ማሻሻል ከምትፈልገው ልማድ አጠገብ ባለው ሣጥን ላይ ምልክት አድርግ።)

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ