የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w24 የካቲት ገጽ 32
  • በሥራ ላይ የምታውላቸውን መንፈሳዊ ዕንቁዎች ፈልግ

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • በሥራ ላይ የምታውላቸውን መንፈሳዊ ዕንቁዎች ፈልግ
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2024
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ለጥናት የሚረዱ ሐሳቦች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2023
  • መጽሐፍ ቅዱስ ሊጠቅመኝ የሚችለው እንዴት ነው?​—ክፍል 1፦ መጽሐፍ ቅዱስን መመርመር
    የወጣቶች ጥያቄ
  • የጥናትህን ውጤት ለሌሎች አካፍል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2025
  • ለጥናት የሚረዱ ሐሳቦች
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2023
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2024
w24 የካቲት ገጽ 32

ለጥናት የሚረዱ ሐሳቦች

በሥራ ላይ የምታውላቸውን መንፈሳዊ ዕንቁዎች ፈልግ

መጽሐፍ ቅዱስን ስናነብ ተጨማሪ ምርምር በማድረግ መንፈሳዊ ዕንቁዎችን መፈለግ እንችላለን። ይሁንና የተሟላ ጥቅም ማግኘት የምንችለው እንዴት ነው?

ጥልቀት ያለው ጥናት አድርግ። ከመጽሐፍ ቅዱስ ዘገባዎች ጋር በተያያዙ ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ምርምር አድርግ። ለምሳሌ ዘገባውን የጻፈው ማን ነው? የተጻፈው ለማን ነው? የተጻፈው መቼ ነው? በወቅቱ የነበረው ሁኔታ ምን ይመስላል? ከዚያ በፊት ምን ተከናውኗል? ከዚያ በኋላስ?

ትምህርቱን ለማስተዋል ሞክር። ይህን ለማድረግ እንደሚከተሉት ባሉ ጥያቄዎች ላይ ምርምር ማድረግ ትችላለህ፦ ‘በዘገባው ላይ የተጠቀሱት ሰዎች ምን ተሰምቷቸዋል? የትኞቹን ባሕርያት አንጸባርቀዋል? እነዚህን ባሕርያት ማዳበር ወይም ከማዳበር መቆጠብ ያለብኝ ለምንድን ነው?’

ትምህርቱን በሥራ ላይ አውል። የተማርከውን ነገር በአገልግሎት ላይ ወይም ከሌሎች ሰዎች ጋር ካለህ ግንኙነት ጋር በተያያዘ በሥራ ላይ አውል። እንዲህ በማድረግ አምላካዊ ጥበብ እንዳለህ ማሳየት ትችላለህ። መጽሐፍ ቅዱስ “ጥበበኛ የሆነ ሁሉ እነዚህን ነገሮች ልብ ይላል” በማለት ይናገራል።—መዝ. 107:43

  • ጠቃሚ ምክር፦ በሳምንቱ መሃል በምናደርገው ስብሰባ ላይ ያለው ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት የሚለው ክፍል በትምህርቱ ተግባራዊነት ላይ እንድናተኩር የሚረዳን እንዴት እንደሆነ ለማስተዋል ሞክር። ይህ ክፍል ራሳችንን ልንጠይቅ የምንችላቸውን ጥያቄዎች፣ ልናሰላስልባቸው የምንችላቸውን ነጥቦች እንዲሁም ትምህርቱን የሚያጎሉ ሥዕሎችን ይዞ ይወጣል።

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ