ለጥናት የሚረዱ ሐሳቦች
የጥናትህን ውጤት ለሌሎች አካፍል
የጥናት ፕሮግራም መንፈሳችንን ያድስልናል፤ ሆኖም ያገኘናቸውን የሚያበረታቱ መንፈሳዊ ዕንቁዎች ለሌሎች ስናካፍል መንፈሳችን ይበልጥ ይታደሳል። ምሳሌ 11:25 “ሌሎችን [የሚያረካ] እሱ ራሱ ይረካል” ይላል።
ያገኘነውን ትምህርት ለሌሎች ስናካፍል ነጥቦቹን በቀላሉ ማስታወስና ግንዛቤያችንን ማሳደግ እንችላለን። ደግሞም እነዚህ ነጥቦች ሌሎችን ስለሚጠቅሙ እንዲህ ያሉትን ዕንቁዎች ለእነሱ በማካፈላችን እንደሰታለን።—ሥራ 20:35
እስቲ እንዲህ ለማድረግ ሞክር፦ በሚቀጥለው ሳምንት፣ የተማርከውን ነገር ለሌላ ሰው ማካፈል የምትችልበት አጋጣሚ ፈልግ። ለቤተሰብህ አባል፣ በጉባኤህ ውስጥ ላለ ሰው፣ ለሥራ ባልደረባህ፣ አብሮህ ለሚማር ልጅ፣ ለጎረቤትህ ወይም በአገልግሎት ላይ ላገኘኸው ሰው መናገር ትችል ይሆናል። ሐሳቡን ባልተወሳሰበና ግልጽ በሆነ መንገድ በራስህ አባባል ለመግለጽ ጥረት አድርግ።
ይህን አስታውስ፦ የተማርከውን ነገር ለሌሎች የምታካፍለው እነሱን ለማስደመም ሳይሆን ለማበረታታት ሊሆን ይገባል።—1 ቆሮ. 8:1