የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • ijwbq ርዕስ 108
  • ትንቢት ምንድን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • ትንቢት ምንድን ነው?
  • የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
  • አምላክ መጽሐፍ ቅዱስን በመንፈስ አነሳሽነት ያስጻፈው እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1997
  • አምላክን አይቶት የሚያውቅ አለ?
    የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
  • አምላክ ማን ነው?
    እውነተኛ እምነት ደስታ ያስገኝልሃል
  • በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ የሰፈረው ሐሳብ ሰዎች ያመነጩት ነው?
    ንቁ!—2007
ለተጨማሪ መረጃ
የመጽሐፍ ቅዱስ ጥያቄዎችና መልሶቻቸው
ijwbq ርዕስ 108
አጥማቂው ዮሐንስ

ትንቢት ምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

ትንቢት በአምላክ መንፈስ መሪነት የሚነገር መልእክት ሲሆን አምላክ ፈቃዱን ለመግለጥ የሚጠቀምበት መንገድ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ነቢያት “ከአምላክ የተቀበሉትን ትንቢት በመንፈስ ቅዱስ ተገፋፍተው” እንደተናገሩ ይገልጻል። (2 ጴጥሮስ 1:20, 21) በመሆኑም ነቢይ፣ የአምላክን መልእክት ተቀብሎ ለሌሎች የሚያስተላልፍ ሰው ነው።—የሐዋርያት ሥራ 3:18

ነቢያት ከአምላክ መልእክት የተቀበሉት እንዴት ነበር?

አምላክ ሐሳቡን ለነቢያት ለማስተላለፍ በተለያዩ ዘዴዎች ተጠቅሟል፦

  • በጽሑፍ። አምላክ ይህን ዘዴ ቢያንስ አንድ ጊዜ ይኸውም በጽሑፍ የሰፈሩትን አሥርቱን ትእዛዛት በቀጥታ ለሙሴ በሰጠበት ወቅት ተጠቅሞበታል።—ዘፀአት 31:18

  • በመላእክት በኩል በመናገር። ለምሳሌ አምላክ፣ ሙሴ ለግብፁ ፈርዖን የሚነገረውን መልእክት ያሳወቀው በአንድ መልአክ አማካኝነት ነው። (ዘፀአት 3:2-4, 10) አምላክ አንድን መልእክት ቃል በቃል መግለጽ ሲፈልግ በመላእክት ይጠቀም ነበር፤ ለሙሴ የሚከተለውን መልእክት በነገረው ጊዜም ያደረገው ይህንኑ ነው፦ “ከአንተም ሆነ ከእስራኤል ጋር ቃል ኪዳን የምገባው በእነዚህ ቃላት መሠረት ስለሆነ እነዚህን ቃላት ጻፍ።”—ዘፀአት 34:27a

  • በራእይ። ነቢያት ንቁ በሆኑበትና ሙሉ በሙሉ ራሳቸውን በሚያውቁበት ሁኔታ ውስጥ ሆነው ራእይ ያዩበት ጊዜ አለ። (ኢሳይያስ 1:1፤ ዕንባቆም 1:1) ራእዩ እውን ከመሆኑ የተነሳ ራእዩን የተመለከተው ነቢይ ተሳትፎ ያደረገባቸው ጊዜያት አሉ። (ሉቃስ 9:28-36፤ ራእይ 1:10-17) በሌሎች ጊዜያት ደግሞ ነቢዩ ራእዩን የሚያየው በሰመመን ውስጥ ሆኖ ሊሆን ይችላል። (የሐዋርያት ሥራ 10:10, 11፤ 22:17-21) አምላክ፣ ነቢዩ ተኝቶ ሳለ በሕልም መልእክቱን የገለጠበት ጊዜም ነበር።—ዳንኤል 7:1፤ የሐዋርያት ሥራ 16:9, 10

  • አስተሳሰብን በመምራት። አምላክ የነቢያቱን አስተሳሰብ በመምራት መልእክቱን አስተላልፏል። “ቅዱሳን መጻሕፍት ሁሉ በአምላክ መንፈስ መሪነት የተጻፉ ናቸው” የሚለው የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስም ይህን ሐሳብ የሚያስተላልፍ ነው። “በአምላክ መንፈስ መሪነት” የሚለው አገላለጽ “አምላክ የተነፈሰበት” ተብሎም ሊተረጎም ይችላል። (2 ጢሞቴዎስ 3:16 ዚ ኤምፋሳይዝድ ባይብል) አምላክ በአገልጋዮቹ አእምሮ ውስጥ የእሱን ሐሳብ “ለመተንፈስ” ቅዱስ መንፈሱን ወይም ኃይሉን ተጠቅሟል። መልእክቱ የአምላክ ቢሆንም ነቢዩ በራሱ አባባል ይገልጸዋል።—2 ሳሙኤል 23:1, 2

ትንቢት የሚያመለክተው ስለ ወደፊቱ ጊዜ የተነገረን ነገር ብቻ ነው?

አይደለም፤ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች ስለ ወደፊቱ ጊዜ ብቻ የተነገሩ አይደሉም። ሆኖም ከአምላክ የሚመጡት አብዛኞቹ መልእክቶች በተዘዋዋሪም ቢሆን ስለ ወደፊቱ ጊዜ ይናገራሉ። ለምሳሌ ያህል፣ የአምላክ ነቢያት እስራኤላውያን መጥፎ መንገዳቸውን እንዲተዉ በተደጋጋሚ አስጠንቅቀው ነበር። እነዚህ ማስጠንቀቂያዎች፣ እስራኤላውያን ማስጠንቀቂያውን ከሰሙ ወደፊት የሚያገኙትን በረከት ካልሰሙ ደግሞ ወደፊት የሚጠብቃቸውን ቅጣት የሚገልጹ ነበሩ። (ኤርምያስ 25:4-6) ውጤቱ እስራኤላውያን ለመከተል በሚመርጡት ጎዳና ላይ የተመካ ነበር።—ዘዳግም 30:19, 20

ስለ ወደፊቱ ጊዜ የማይናገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች

  • በአንድ ወቅት እስራኤላውያን አምላክ እንዲረዳቸው ጠየቁ፤ በዚህ ጊዜ አምላክ በአንድ ነቢይ አማካኝነት ትእዛዛቱን ስላልጠበቁ እንደማይረዳቸው ገልጾላቸዋል።—መሳፍንት 6:6-10

  • ኢየሱስ ከሳምራዊቷ ሴት ጋር ሲወያይ ስላሳለፈችው ሕይወት ነግሯት ነበር፤ ይህን ሊያውቅ የሚችለው በመለኮታዊ እርዳታ ብቻ ነው። ስለ ወደፊቱ ጊዜ የተናገረው ነገር ባይኖርም እንኳ ነቢይ እንደሆነ ተገንዝባለች።—ዮሐንስ 4:17-19

  • ኢየሱስ ለፍርድ በቀረበበት ጊዜ ጠላቶቹ ፊቱን ሸፍነው እየመቱት “እስቲ ትንቢት ተናገር! የመታህ ማን ነው?” እያሉ ይጠይቁት ነበር። በዚህ ወቅት ኢየሱስን የጠየቁት ስለ ወደፊቱ ጊዜ እንዲናገር ሳይሆን ማን እንደመታው በመለኮታዊ እርዳታ እንዲነግራቸው ነበር።—ሉቃስ 22:63, 64

a በዚህ ወቅት አምላክ ሙሴን በቀጥታ ያነጋገረው ሊመስል ቢችልም አምላክ የሕጉን ቃል ኪዳን ለማስተላለፍ በመላእክት እንደተጠቀመ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል።—የሐዋርያት ሥራ 7:53፤ ገላትያ 3:19

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ