መዝሙር 6
የአምላክ አገልጋይ ጸሎት
በወረቀት የሚታተመው
1. ሉዓላዊው ይሖዋ አባት፣
ታላቅ ስምህ ይታወቅ በስፋት።
ምሕረትህ ምንጊዜም አያልቅም፤
ጸንቶ ይኖራል ለዘላለም።
ይኖራል ለዘላለም፤
ምሕረትህ አያልቅ መቼም።
2. የ’ውነትን ፍቅር ትከልብን።
እርዳን እንድናደርግ ፈቃድህን፤
እንድንፈጽም ት’ዛዝህን፤
እንድንፈልግ በጎችህን።
እንመግብ በጎችህን፤
እናክብር ት’ዛዝህን።
3. የሰማዩን ጥበብ ለግሰን፤
ባንተ ፍቅር ይሞላ ልባችን።
እርዳን እናሳይ ምሕረት፣ ፍቅር፣
ቅን የሆኑትን ስናስተምር።
ሰዎችን ስናስተምር፣
እናሳይ ምሕረት፣ ፍቅር።
(በተጨማሪም መዝ. 143:10ን፣ ዮሐ. 21:15-17ን እና ያዕ. 1:5ን ተመልከት።)