መዝሙር 91
አባቴ፣ አምላኬና ወዳጄ
በወረቀት የሚታተመው
1. መኖር በዚህ ዓለም ውስጥ፣
ብዙ ነው ሥቃዩ፣ መከራው።
ሆኖም ሁሌ እላለሁ፦
“መኖሬ ዋጋ ’ለው።”
(አዝማች)
ዓመፅ የለም ባምላክ ዘንድ፤
መቼም ቢሆን ፍቅሬን አይረሳም።
ብቻዬን አይደለሁም፤
ካጠገቤ አለ ሁሌም።
እሱ ጠባቂዬ ነው፤
ይንከባከበኛል ምንጊዜም።
አባቴና አምላኬ ነው፤
ወዳጄም ነው።
2. ወጣትነቴ አልፎ፣
የጭንቀት ዘመን መጥቶብኛል።
ቢሆንም በ’ምነት ዓይኔ
ተስፋው ይታየኛል።
(አዝማች)
ዓመፅ የለም ባምላክ ዘንድ፤
መቼም ቢሆን ፍቅሬን አይረሳም።
ብቻዬን አይደለሁም፤
ካጠገቤ አለ ሁሌም።
እሱ ጠባቂዬ ነው፤
ይንከባከበኛል ምንጊዜም።
አባቴና አምላኬ ነው፤
ወዳጄም ነው።
(በተጨማሪም መዝ. 71:17, 18ን ተመልከት።)