መዝሙር 83
ራሳችንን መግዛት ያስፈልገናል
በወረቀት የሚታተመው
1. ከልብ ብንወደውም ይሖዋን፣
ራሳችንን ’ንግዛ ኃጢያት አለብን።
ስለ ሥጋ ማሰብ ጥፋት ነው፤
ስለ መንፈስ ማሰብ ሕይወት ነው።
2. ሰይጣን ሁልጊዜ ይፈትነናል፤
ያለብን ኃጢያትም ያሳስተናል።
የ’ውነት ኃይል ከኃጢያት ይበልጣል፤
’ናሸንፋለን በአምላክ ኃይል።
3. ምግባር፣ ቃላችን ይነካል ስሙን፤
እንጣር ነቀፋ እንዳይኖርብን።
ለዘላለም ይሁን ግባችን፣
ምንጊዜም መግዛት ራሳችንን።
(በተጨማሪም 1 ቆሮ. 9:25ን፣ ገላ. 5:23ን እና 2 ጴጥ. 1:6ን ተመልከት።)