የቲኦክራሲያዊ አገልግሎት ትምህርት ቤት ክለሳ
የካቲት 22, 2010 በሚጀምር ሳምንት በቲኦክራሲያዊ የአገልግሎት ትምህርት ቤት ላይ መልስ የሚሰጥባቸው ጥያቄዎች የሚከተሉት ናቸው። የትምህርት ቤቱ የበላይ ተመልካች ከጥር 4 እስከ የካቲት 22, 2010 ድረስ ባሉት ሳምንታት ውስጥ በቀረቡት ክፍሎች ላይ የተመሠረተ የ20 ደቂቃ ክለሳ ይመራል።
1. የትኛው ዝንባሌ እንዳይጠናወተን መጠንቀቅ አለብን? (ኢያሱ 22:9-12, 21-33) [w04 12/1 ገጽ 12 አን. 3]
2. ኢያሱ፣ በኢያሱ 24:14, 15 ላይ ያለውን ሐሳብ እንዲናገር ያነሳሳው ምን መሆን አለበት? ይህስ ለእኛ ምን ትምህርት ይዞልናል? [w08 5/15 ከገጽ 17-18 ከአን. 4-6]
3. የበኣል አምላኪዎችና የአምልኮ ሥርዓታቸው ለእስራኤላውያን ወጥመድ የሆነበት አንዱ መንገድ ምንድን ነው? (መሳ. 2:3) [w08 2/15 ገጽ 27 ከአን. 2-3]
4. ናዖድ በሰይፍ አጠቃቀሙ ረገድ ካሳየው ድፍረት ምን ትምህርት እናገኛለን? (መሳ. 3:16, 21) [w97 3/15 ገጽ 31 አን. 4]
5. ይሖዋ ጌዴዎንን እና አብረውት የነበሩትን 300 ሰዎች ስላዳነበት መንገድ ስናጠና ምን ማበረታቻ እናገኛለን? (መሳ. 7:19-22) [w05 7/15 ገጽ 16 አን. 8]
6. የይሖዋ ነፍስ ‘ስለ እስራኤል ጉስቁልና ያዘነው’ እንዴት ነው? (መሳ. 10:16 የ1954 ትርጉም) [cl ከገጽ 254-255 ከአን. 10-11]
7. ዮፍታሔ የተሳለው የሰው መሥዋዕት ለማቅረብ ነበር? (መሳ. 11:30, 31) [w05 1/15 ገጽ 26 አን. 1]
8. የሳምሶን ኃይል ቃል በቃል በፀጉሩ ላይ ነበር? (መሳ. 16:18-20) [w05 3/15 ገጽ 28 አን. 5-6]
9. በመሳፍንት 16:3 ላይ ስለተገለጸው የሳምሶን አስገራሚ ድርጊት የበለጠ እውቀት ማግኘታችን የሚጠቅመን እንዴት ነው? [w04 10/15 ገጽ 15 ከአን. 7-8]
10. ‘እያንዳንዱ ሰው ለራሱ መልካም መስሎ የታየውን ማድረጉ’ ሥርዓት አልበኝነት እንዲነግሥ አላደረገም? (መሳ. 17:6) [w05 1/15 ገጽ 27]