መዝሙር 53
በአንድነት አብሮ መሥራት
በወረቀት የሚታተመው
(ኤፌሶን 4:3)
1. አምላክ ጠራን ወደ ቤቱ።
ተፈጸመልን ትንቢቱ።
ሰላም አንድነት አገኘን፤
በደስታም ተሞላን።
አንድነታችንን እናደንቃለን።
ያምላክ ሥራ በዝቶልናል።
ልጁ ’ንዲመራን ተሹሟል።
በታዛዥነት አንድ ሆነን፣
’ናገልግል ይሖዋን።
2. ስንጸልይ ላንድነታችን፣
ስንጥር ደጎች ለመሆን፣
ያድጋል፣ ይበዛል ፍቅራችን፤
ደስታ፣ ሰላማችን።
ሰላም ያስደስታል፤
ልብ ያሳርፋል።
ወንድሞችን ከወደድን፣
እናገኛለን ሰላምን።
ባምላክ እርዳታ ተባብረን
’ናገለግላለን።
(በተጨማሪም ሚክ. 2:12ን፣ ሶፎ. 3:9ን እና 1 ቆሮ. 1:10ን ተመልከት።)