መዝሙር 41
በወጣትነታችሁ ይሖዋን አምልኩ
በወረቀት የሚታተመው
1. ወጣቶች አምላክ ይወዳችኋል፤
ከፍ ያለ ቦታም ይሰጣችኋል።
በቤተሰብ፣ በወንድሞች በኩል፣
አሳቢነቱን ያሳያችኋል።
2. ወላጆቻችሁን አክብሯቸው፤
ይወዷችኋል አታስከፏቸው።
በአምላክ ፊት ሞገስ ካገኛችሁ፣
እጅግ ደስተኛ ትሆናላችሁ።
3. ይሖዋን አስቡ ልጅ ሳላችሁ፤
ለእውነትም ፍቅር ይኑራችሁ።
ይሖዋን በቅንዓት ብታመልኩ፣
በምርጫችሁ ደስ ይሰኛል ልቡ።