መዝሙር 71
የአምላክ ስጦታ የሆነው መንፈስ ቅዱስ
በወረቀት የሚታተመው
1. ልዑሉ አምላክ፣ መሐሪው አባት፣
ከልባችን ይበልጥ ታላቅ ነህ።
ሸክማችንን ቀላል አ’ርግልን፤
አጽናኝ መንፈስህን ስጠን ’ባክህ።
2. ልናንጸባርቅ አንችል ክብርህን፤
ብዙ ጊዜ እንስታለን።
አምላክ ሆይ፣ እንማጸንሃለን፣
መንፈስህ በየቀኑ ’ንዲመራን።
3. ስንዝል፣ ስንደክም፣ ተስፋ ስንቆርጥ፣
መንፈስህ ነው እኛን ’ሚያድሰን።
እንደ ንስር መብረር እንድንችል፣
ኃያል ቅዱስ መንፈስህን ስጠን