መዝሙር 38
ሸክማችሁን በይሖዋ ላይ ጣሉ
በወረቀት የሚታተመው
(መዝሙር 55)
1. ይሖዋ ሆይ፣ ተለመነኝ፤
እባክህ ተመልከተኝ።
ለጸሎቴ ምላሽ ስጠኝ፤
ደፋር እንድሆን እርዳኝ።
(አዝማች)
ሸክምህን ባምላክ ላይ ጣል፤
እሱ ይደግፍሃል።
እንድትናወጥ አይፈቅድም፤
አጽንቶ ያቆምሃል።
2. ምነው የርግብ ክንፍ በኖረኝ፣
በርሬ ባመለጥኩኝ።
ሊጎዱኝ ከሚፈልጉ
ከሚጠሉኝ በዳንኩኝ።
(አዝማች)
ሸክምህን ባምላክ ላይ ጣል፤
እሱ ይደግፍሃል።
እንድትናወጥ አይፈቅድም፤
አጽንቶ ያቆምሃል።
3. ወደ ይሖዋ ’ጮሃለሁ፤
ጥበቃውን እሻለሁ።
እሱ ሰላምን ይሰጣል፤
ቅኖችን ያበረታል።
(አዝማች)
ሸክምህን ባምላክ ላይ ጣል፤
እሱ ይደግፍሃል።
እንድትናወጥ አይፈቅድም፤
አጽንቶ ያቆምሃል።
(በተጨማሪም መዝ. 22:5ን እና መዝ. 31:1-24ን ተመልከት።)