የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp16 ቁጥር 5 ገጽ 16
  • የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2016
  • ንዑስ ርዕሶች
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?
  • የአምላክ መንግሥት የሚመጣው መቼ ነው?
  • የአምላክ መንግሥት
    ንቁ!—2013
  • የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2020
  • ምድራችንን ማስተዳደር የሚችል የተረጋጋ መንግሥት አለ?—መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
    ተጨማሪ ርዕሰ ጉዳዮች
  • የአምላክን መንግሥት በተመለከተ እውነቱ ምንድን ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2020
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2016
wp16 ቁጥር 5 ገጽ 16
በሰማይ ላይ ካለ ዙፋን ወደ ምድር የሚፈነጥቅ ብርሃን

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ያስተምራል?

የአምላክ መንግሥት ምንድን ነው?

ሰዎች ምን ብለው ያምናሉ? አምላክ በሰው ልብ ውስጥ እንደሚገዛ የሚያመለክት ነገር ነው የሚሉ አሉ፤ ሌሎች ደግሞ ሰዎች ዓለም አቀፍ ሰላምና ወንድማማችነት ለማምጣት በሚያደርጉት ጥረት የሚገኝ ነገር እንደሆነ ያስባሉ። እርስዎስ ስለዚህ ጉዳይ ምን አመለካከት አለዎት?

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

“የሰማይ አምላክ ፈጽሞ የማይጠፋ መንግሥት ያቋቁማል። ይህም መንግሥት . . . እነዚህን [ሰብዓዊ] መንግሥታት ሁሉ ያደቅቃል፤ ፈጽሞም ያጠፋቸዋል።” (ዳንኤል 2:44) የአምላክ መንግሥት እውን መስተዳድር ነው።

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ሌላስ ነገር አለ?

  • የአምላክ መንግሥት የሚገዛው በሰማይ ሆኖ ነው።—ማቴዎስ 10:7፤ ሉቃስ 10:9

  • አምላክ በዚህ መንግሥት አማካኝነት በሰማይም ሆነ በምድር ላይ ፈቃዱ እንዲፈጸም ያደርጋል። —ማቴዎስ 6:10

የአምላክ መንግሥት የሚመጣው መቼ ነው?

ምን ትላለህ?

  • ማንም አያውቅም

  • በቅርቡ ይመጣል

  • ፈጽሞ አይመጣም

መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

“ይህ የመንግሥቱ ምሥራች ለብሔራት ሁሉ ምሥክር እንዲሆን በመላው ምድር ይሰበካል፤ ከዚያም መጨረሻው ይመጣል።” (ማቴዎስ 24:14) ምሥራቹ በተሟላ መልኩ ከተሰበከ በኋላ የአምላክ መንግሥት አሁን ያለውን ክፉ ሥርዓት ያጠፋል።

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረው ሌላስ ነገር አለ?

  • በምድር ላይ ያለ ማንም ሰው የአምላክ መንግሥት የሚመጣበትን ጊዜ በትክክል አያውቅም።—ማቴዎስ 24:36

  • የመጽሐፍ ቅዱስ ትንቢቶች መንግሥቱ በቅርቡ እንደሚመጣ ይጠቁማሉ።—ማቴዎስ 24:3, 7, 12

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት በይሖዋ ምሥክሮች የተዘጋጀውን ትክክለኛው የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ምንድን ነው? የሚል ርዕስ ያለውን የዚህን መጽሐፍ ምዕራፍ 8 ተመልከት

መጽሐፉ www.jw.org/am ላይም ይገኛል

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ