ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | ሕዝቅኤል 46-48
እስራኤላውያን ወደ አገራቸው ሲመለሱ ያገኟቸው በረከቶች
ሕዝቅኤል ስለ ቤተ መቅደሱ ያየው ራእይ በምርኮ ያሉትን እስራኤላውያን አበረታቷቸዋል፤ እንዲሁም ወደ አገራቸው እንደሚመለሱ አስቀድመው የተነገሩት ትንቢቶች እንደሚፈጸሙ አረጋግጦላቸዋል። ንጹሑ አምልኮ ይሖዋ በባረካቸው ሰዎች ሕይወት ውስጥ ትልቅ ቦታ ይኖረዋል።
ራእዩ ሕዝቡ እንደሚደራጅ፣ እንደሚደጋገፍና ያለ ስጋት እንደሚኖር ተስፋ ይሰጣል
ምድሪቱ ለምለምና ፍሬያማ ትሆናለች
እያንዳንዱ ቤተሰብ የራሱ ርስት ይኖረዋል
መሬቱ ለሕዝቡ ከመከፋፈሉ በፊት ለይሖዋ “መዋጮ” ሆኖ የሚሰጥ ልዩ መሬት ‘ተለይቶ’ ተቀምጧል
በሕይወቴ ውስጥ ቅድሚያ የምሰጠው ለይሖዋ አምልኮ እንደሆነ ማሳየት የምችለው እንዴት ነው? (w06 4/15 27-28 አን. 13-14)