ክርስቲያናዊ ሕይወት
መለኮታዊውን ትምህርት ተከታተሉ
አስፈላጊ የሆነው ለምንድን ነው? ታላቅ አስተማሪ የሆነው ይሖዋ ከሁሉ የላቀ ትምህርት አዘጋጅቶልናል። የተሻለ ሕይወት ለመምራት የሚያስችለን እንዲሁም አስደናቂ የወደፊት ሕይወት ለማግኘት የሚረዳን ትምህርት በነፃ አቅርቦልናል! (ኢሳ 11:6-9፤ 30:20, 21፤ ራእይ 22:17) ከይሖዋ የምንቀስመው መለኮታዊ ትምህርት፣ ሕይወት አድን የሆነውን መልእክት ለሌሎች ለማካፈልም ያሠለጥነናል።—2ቆሮ 3:5
ይህን ማድረግ የሚቻለው እንዴት ነው?
ትሕትናን እና የዋህነትን አዳብሩ።—መዝ 25:8, 9
ይሖዋ በአሁኑ ወቅት ከሚሰጠን ሥልጠና ለመጠቀም ጥረት አድርጉ፤ ለምሳሌ በሳምንቱ መካከል በሚደረገው ስብሰባ ላይ የተማሪ ክፍል ማቅረብ ትችላላችሁ
ልትደርሱባቸው የምትችሉ መንፈሳዊ ግቦች አውጡ።—ፊልጵ 3:13
ተጨማሪ ሥልጠናዎች ለማግኘት ብቃቱን እንድታሟሉ በሕይወታችሁ ውስጥ አንዳንድ ማስተካከያዎችን አድርጉ።—ፊልጵ 3:8
ከይሖዋ በመማር መንፈሳዊ ብልጽግና ማግኘት የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
አንዳንድ አስፋፊዎች በመንግሥቱ ወንጌላውያን ትምህርት ቤት ለመካፈል ሲሉ የትኞቹን እንቅፋቶች መወጣት አስፈልጓቸዋል?
በመንግሥቱ ወንጌላውያን ትምህርት ቤት የሚካፈሉ ተማሪዎች ምን ጥቅሞች ያገኛሉ?
ተመራቂዎቹ በአዲሱ የአገልግሎት ምድባቸው ሲያገለግሉ የጉባኤያቸው አባላት የረዷቸው እንዴት ነው?
በመንግሥቱ ወንጌላውያን ትምህርት ቤት ለመካፈል መሟላት የሚያስፈልጋቸው ብቃቶች የትኞቹ ናቸው? (kr 189)
በይሖዋ ድርጅት ውስጥ ልታገኛቸው የምትችላቸው ምን ሌሎች ሥልጠናዎች አሉ?
መለኮታዊውን ትምህርት መከታተልህ ምን በረከቶች ያስገኝልሃል?