ከአምላክ ቃል የሚገኝ ውድ ሀብት | 2 ቆሮንቶስ 4-6
“ተስፋ አንቆርጥም”
በአንድ ያረጀ ሕንፃ ላይ የሚኖሩ ሁለት ቤተሰቦችን በዓይነ ሕሊናችሁ ለመመልከት ሞክሩ። አንደኛው ቤተሰብ በሁኔታው በጣም ተማርሯል። ሌላኛው ቤተሰብ ግን ደስተኛ ነው። ይህ የሆነው ለምንድን ነው? የሁለተኛው ቤተሰብ አባላት በቅርቡ አዲስና የሚያምር ቤት ውስጥ እንደሚገቡ ስለሚያውቁ ነው።
“ፍጥረት ሁሉ እስካሁን ድረስ አብሮ በመቃተትና በመሠቃየት ላይ እንደሚገኝ እናውቃለን”፤ የአምላክ አገልጋዮች ግን ብርታት የሚሰጥ ተስፋ አላቸው። (ሮም 8:22) አሁን የሚደርስብን መከራ፣ ሌላው ቀርቶ ለበርካታ አሥርተ ዓመታት ሲያሠቃዩን የቆዩት ችግሮች እንኳ አምላክ በሚያመጣው አዲስ ዓለም ውስጥ ለዘላለም ከምናገኘው በረከት አንጻር ሲታዩ “ጊዜያዊና ቀላል” ናቸው። የአምላክ መንግሥት ወደፊት በሚያመጣቸው በረከቶች ላይ ትኩረት ማድረጋችን ደስተኞች እንድንሆንና ተስፋ እንዳንቆርጥ ይረዳናል።