ክርስቲያናዊ ሕይወት
መስበክና ማስተማር ትችላላችሁ!
መጀመሪያ ላይ ሙሴ ይሖዋ የሰጠውን ኃላፊነት ለመወጣት ብቃቱ እንዳለው አልተሰማውም ነበር። (ዘፀ 4:10, 13) አንተስ እንደዚህ ተሰምቶህ ያውቃል? ከይሖዋ ምሥክሮች ጋር መጽሐፍ ቅዱስን እያጠናህ ነው? መቼም ቢሆን ከቤት ወደ ቤት መስበክ እንደማትችል ተሰምቶህ ያውቃል? ወይም ትምህርት ቤት ውስጥ መመሥከር የሚከብድህ ወጣት ልትሆን ትችላለህ። አሊያም ደግሞ በስልክ መስበክ ወይም በአንድ ዓይነት የአደባባይ ምሥክርነት ዘርፍ መካፈል ያስፈራህ ይሆናል። ከሆነ ይሖዋ መንፈስ ቅዱስን እንዲሰጥህ በጸሎት ለምነው። (1ጴጥ 4:11) ይሖዋ እሱ የሰጠህን የትኛውንም ኃላፊነት ለመወጣት እንደሚረዳህ መተማመን ትችላለህ።—ዘፀ 4:11, 12
ደፋር ሁኑ!—አስፋፊዎች የሚለውን ቪዲዮ ተመልከት፤ ከዚያም የሚከተሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ ሞክር፦
እህት አዎያማ ምን ተፈታታኝ ሁኔታ አጋጥሟት ነበር?
ብርታትና ድፍረት ማግኘት የቻለችው እንዴት ነው?—ኤር 20:7-9
በይሖዋ አገልግሎት ይበልጥ ለመካፈል ራሷን በማቅረቧ ምን ጥቅም አግኝታለች?
ይሖዋ በአገልግሎት ላይ የሚያጋጥሙህን የትኞቹን ፈተናዎች እንድትወጣ ሊረዳህ ይችላል?