የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • g 4/08 ገጽ 26
  • የማጣበቅ ባሕርይ ያለው የጌኮ እግር

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • የማጣበቅ ባሕርይ ያለው የጌኮ እግር
  • ንቁ!—2008
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ፍጥረት የይሖዋን ጥበብ በግልጽ ያሳያል
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ተፈጥሮ ምን ያስተምረናል?
    ንቁ!—2006
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2008
  • የመጀመሪያውን ንድፍ ያወጣው ማን ነው?
    ሕይወት የተገኘው በፍጥረት ነው?
ለተጨማሪ መረጃ
ንቁ!—2008
g 4/08 ገጽ 26

ንድፍ አውጪ አለው?

የማጣበቅ ባሕርይ ያለው የጌኮ እግር

◼ የሳይንስ ሊቃውንት፣ ጌኮ በኮርኒስ ላይ ተገልብጦ መሮጥን ጨምሮ ልሙጥና ለስላሳ በሆኑ ነገሮች ላይ በመሄድ ችሎታው በእጅጉ ይደነቃሉ! አስገራሚ የሆነው ይህ ትንሽ እንሽላሊት እንዲህ እንዲያደርግ ያስቻለው ምንድን ነው?

መጽሐፍ ቅዱስ እንሽላሊት “በእጆቿ ሙጭጭ አድርጋ ትይዛለች” በማለት ይናገራል። (ምሳሌ 30:28 NW) በእርግጥም የእንሽላሊት እግሮች እጅ የሚመስሉ ሲሆን ልሙጥና ለስላሳ የሆኑ ነገሮችን ሙጭጭ አድርገው የመያዝ አስገራሚ ችሎታ አላቸው። እያንዳንዱ ጣት እንደ ተረተር ያሉ በሺህ የሚቆጠሩ ጉብታ መሰል ነገሮች አሉት። እያንዳንዱ ጉብታ ደግሞ በዓይን የማይታዩ በመቶ የሚቆጠሩ ፀጉር መሰል ጭረቶች አሉት። እነዚህ ፀጉር መሰል ጭረቶች እርስ በርስ በመሳሳብ የሚያመነጩት ኃይል (ቫን ደር ዋልስ ተብሎ ይጠራል) እንሽላሊቱ በመስተዋት ላይ ተገልብጦ በሚሮጥበት ጊዜም እንኳ ክብደቱን የመሸከም አቅም አለው!

ተመራማሪዎች እንደ ጌኮ እግሮች ልሙጥና ለስላሳ በሆኑ ነገሮች ላይ መጣበቅ የሚችል ፕላስተር የመሥራት ፍላጎት አላቸው።a ሳይንስ ኒውስ የተሰኘ አንድ መጽሔት እንዲህ ዓይነቱ ፕላስተር “በሕክምናው መስክ ዘርፈ ብዙ ጥቅም” ሊሰጥ እንደሚችል ዘግቧል። ለምሳሌ ያህል፣ “እርጥበት ቢያገኘውም እንኳ ከታሰረበት ቁስል የማይፈታ ፋሻ” ወይም “በቀዶ ሕክምና ወቅት የተከፈተን ቆዳ በመስፋት ፋንታ አጣብቆ ሊይዝ የሚችል ፕላስተር” ሆኖ ሊያገለግል ይችላል።

ይህን አጭር ማብራሪያ ካነበብክ በኋላ ምን መደምደሚያ ላይ ደረስክ? የማጣበቅ ባሕርይ ያለው የጌኮ እግር የተገኘው በአጋጣሚ ነው? ወይስ ንድፍ አውጪ አለው?

[የግርጌ ማስታወሻ]

a ከዚህም በተጨማሪ ሳይንቲስቶች ማስል የሚባሉ ትንንሽ የባሕር ፍጥረታት እርጥበት ባላቸው ነገሮች ላይ ለመጣበቅ ሲሉ በሚያመነጩት የፕሮቲን ይዘት ባለው ፈሳሽ ላይ ምርምር እያደረጉ ነው።

[በገጽ 26 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

በሃንጋሪ የሚገኝ ጌኮ ተገልብጦ ሲታይ

[በገጽ 26 ላይ የሚገኝ ሥዕል]

በጌኮ እግር ላይ ያሉ በአጉሊ መነጽር ብቻ የሚታዩ ፀጉር መሰል ነገሮች

[በገጽ 26 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

Gecko: Breck P. Kent; close-up: © Susumu Nishinaga/Photo Researchers, Inc.

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ