የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • w10 5/1 ገጽ 3
  • አምላክ የት ነበር?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • አምላክ የት ነበር?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2006
  • የርዕስ ማውጫ
    ንቁ!—2003
  • የመኖሪያ ቤት እጦት መንስኤው ምንድን ነው?
    ንቁ!—2005
  • የሽብርተኞች ጥቃት ሰለባ የሆኑ ልጆች
    ንቁ!—2006
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2010
w10 5/1 ገጽ 3

አምላክ የት ነበር?

መስከረም 11, 2001፦ ከጠዋቱ 2:46 ላይ አንድ አውሮፕላን በኒው ዮርክ ሲቲ ከሚገኘው ዓለም አቀፍ የንግድ ማዕከል የሰሜኑ ሕንፃ ጋር ተላተመ፤ ይህ አሸባሪዎች በተከታታይ ለመፈጸም ከወጠኑት ጥቃት የመጀመሪያው ነበር። ከዚያም በቀጣዮቹ 102 ደቂቃዎች ውስጥ ወደ 3,000 የሚሆኑ ሰዎች አለቁ።

ታኅሣሥ 26, 2004

በሕንድ ውቅያኖስ ላይ በሬክተር ስኬል ሲለካ 9.0 የደረሰ የመሬት መንቀጥቀጥ በድንገት በመከሰቱ ወደ 5,000 ኪሎ ሜትር ገደማ ርቀት ላይ የምትገኘውን አፍሪካን ጨምሮ 11 አገሮች አደገኛ በሆነ ማዕበል ተመቱ። በአንድ ቀን ውስጥ 150,000 የሚሆኑ ሰዎች ሞተዋል አሊያም የደረሱበት ጠፍቷል፤ ከአንድ ሚሊዮን የሚበልጡ ሰዎች ደግሞ ቤት ንብረታቸውን አጥተዋል።

ነሐሴ 1, 2009፦ አንድ የ42 ዓመት ሰው ከ5 ዓመት ልጁ ጋር በአንዲት አነስተኛ ፈጣን የሞተር ጀልባ ሲከንፉ በእንጨት ከተሠራ ወደብ ጋር ተጋጩ። አባትየው ወዲያውኑ ሲሞት ልጁ ለጊዜው በሕይወት ቢተርፍም በሚቀጥለው ቀን አረፈ። በሐዘኑ የተደቆሰች አንዲት ዘመዳቸው “አንድ ተአምር ተፈጥሮ ልጁ እንደሚተርፍ ተስፋ አድርገን ነበር” ብላለች።

አሸባሪዎች ስለፈጸሙት ጥቃት ወይም ስለ ተፈጥሮ አደጋ ስታነብ አሊያም አንድ አሳዛኝ ሁኔታ ሲያጋጥምህ ‘ይህን ነገር አምላክ እየተመለከተው ይሆን?’ ብለህ አስበህ ታውቃለህ? እንዲሁም ‘አምላክ ትቶን ይሆን?’ ብለህ ራስህን ጠይቀህ ታውቃለህ? በቀጣዩ ርዕስ ላይ እንደምንመለከተው መጽሐፍ ቅዱስ ለእነዚህ ጥያቄዎች የሚያጽናና መልስ ይዟል።

[በገጽ 3 ላይ የሚገኝ የሥዕል ምንጭ]

© Dieter Telemans/Panos Pictures

PRAKASH SINGH/AFP/Getty Images

© Dieter Telemans/Panos Pictures

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ