የመጠበቂያ ግንብ የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
መጠበቂያ ግንብ
የኢንተርኔት ቤተ መጻሕፍት
አማርኛ
፦
  • ፡
  • መጽሐፍ ቅዱስ
  • የሕትመት ውጤቶች
  • ስብሰባዎች
  • wp17 ቁጥር 5 ገጽ 3
  • መላእክት በሕይወትህ ላይ ተጽዕኖ ማሳደር ይችላሉ?

በዚህ ክፍል ውስጥ ምንም ቪዲዮ አይገኝም።

ይቅርታ፣ ቪዲዮውን ማጫወት አልተቻለም።

  • መላእክት በሕይወትህ ላይ ተጽዕኖ ማሳደር ይችላሉ?
  • የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017
  • ተመሳሳይ ሐሳብ ያለው ርዕስ
  • ጠባቂ መልአክ አለህ?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017
  • መላእክት ሊረዱህ የሚችሉት እንዴት ነው?
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—1998
  • መላእክት—“የሕዝብ አገልጋዮች የሆኑ መናፍስት”
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ—2009
  • ታማኝ መላእክትን ምሰሉ
    የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (የጥናት እትም)—2025
ለተጨማሪ መረጃ
የይሖዋን መንግሥት የሚያስታውቅ መጠበቂያ ግንብ (ለሕዝብ የሚሰራጭ)—2017
wp17 ቁጥር 5 ገጽ 3
አንድ ባልና ሚስት በመጽሐፍ ቅዱስ ተጠቅመው አንዲትን ሴት ሲያጽናኑ

የሽፋኑ ርዕሰ ጉዳይ | መጽሐፍ ቅዱስ ስለ መላእክት ምን ይላል?

መላእክት በሕይወትህ ላይ ተጽዕኖ ማሳደር ይችላሉ?

በኩራሳው የሚኖሩት ኬነት እና ፊሎሜና አንድ እሁድ ከሰዓት መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስጠኗቸውን ባልና ሚስት ለመጠየቅ ሄዱ።

ኬነት እንዲህ ብሏል፦ “እዚያ ስንደርስ ቤቱ ዝግ ነበር፣ መኪናቸውም የለም። ሆኖም ለሚስትየዋ ስልክ እንድደውልላት የሆነ ነገር ገፋፋኝ።”

ሴትየዋም ስልኳን አንስታ ባሏ ሥራ መሄዱን ነገረቻቸው። ሆኖም ኬነትና ፊሎሜና ወደ ቤቷ መምጣታቸውን ስታውቅ በሩን ከፍታ አስገባቻቸው።

እነሱም ገና ሲያዩዋት ስታለቅስ እንደነበር ገባቸው። ኬነት የመጽሐፍ ቅዱስ ጥናቱን ከመጀመራቸው በፊት ሲጸልይ ሴትየዋ እንደገና ማልቀስ ጀመረች። ስለዚህ ኬነትና ፊሎሜና የምታለቅሰው ለምን እንደሆነ በደግነት ጠየቋት።

ሴትየዋም ራሷን ለመግደል አስባ እንደነበረና ኬነት የደወለው ራሷን መግደሏን የሚገልጽ ማስታወሻ ለባሏ እየጻፈች በነበረበት ጊዜ እንደሆነ ነገረቻቸው። በመንፈስ ጭንቀት እየተሠቃየች መሆኑን ስትነግራቸው ከመጽሐፍ ቅዱስ ላይ አንዳንድ አጽናኝ ሐሳቦችን አካፈሏት። የሰጧት ማበረታቻ ሕይወቷን አትርፎላታል።

ኬነት “ይሖዋ፣ ይህችን የተጨነቀች ሴት እንድንረዳ ስለፈቀደልን በተለይም ደግሞ በአንድ መልአክ ወይም በቅዱስ መንፈሱ አማካኝነት ስልክ እንድንደውልላት ስላነሳሳን አመሰገንነው!” ብሏል።a

ኬነትና ፊሎሜና፣ አምላክ በአንድ መልአክ ወይም በቅዱስ መንፈሱ አማካኝነት እንደመራቸው ማመናቸው ትክክል ነው? ወይስ ኬነት ልክ በዚያ ሰዓት ስልክ የደወለው እንዲሁ በአጋጣሚ ነው?

ይህን በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም። ይሁን እንጂ፣ አምላክ ለሰዎች መንፈሳዊ እርዳታ ለመስጠት በመላእክቱ እንደሚጠቀም እናውቃለን። ለምሳሌ ያህል፣ አምላክ መንፈሳዊ መመሪያ ያስፈልገው የነበረን አንድ ኢትዮጵያዊ ባለሥልጣን ለመርዳት በአንድ መልአክ እንደተጠቀመ መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፤ መልአኩ ወንጌላዊው ፊልጶስን ከዚህ ሰው ጋር እንዲገናኝ ረድቶታል።—የሐዋርያት ሥራ 8:26-31

የተለያዩ ሃይማኖቶች ከሰው በላይ የሆነ ኃይል ያላቸው መንፈሳዊ ፍጥረታት እንዳሉ ያስተምራሉ፤ እነዚህ ሃይማኖቶች፣ አንዳንዶቹ መንፈሳዊ ፍጥረታት የአምላክን ፈቃድ የሚፈጽሙ ወይም ለሰዎች የግል ጠባቂ ሆነው የሚያገለግሉ ጥሩ መላእክት እንደሆኑ ይናገራሉ። ብዙ ሰዎች መላእክት መኖራቸውን ብቻ ሳይሆን እነዚህ መላእክት በሕይወታቸው ላይ ትልቅ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ ጭምር ያምናሉ። ይሁን እንጂ መላእክት መኖራቸውን የማይቀበሉ በርካታ ሰዎችም አሉ።

መላእክት በእርግጥ አሉ? ከሆነ ደግሞ የመጡት ከየት ነው? መላእክትን በተመለከተ እውነታው ምንድን ነው? ሊጎዱህ ወይም ሊጠቅሙህ ይችላሉ? እስቲ ማስረጃዎቹ ምን እንደሚያሳዩ እንመርምር።

a መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው የአምላክ ስም ይሖዋ ነው።—መዝሙር 83:18

    አማርኛ ጽሑፎች (1991-2025)
    ውጣ
    ግባ
    • አማርኛ
    • አጋራ
    • የግል ምርጫዎች
    • Copyright © 2025 Watch Tower Bible and Tract Society of Pennsylvania
    • የአጠቃቀም ውል
    • ሚስጥር የመጠበቅ ፖሊሲ
    • ሚስጥር የመጠበቅ ማስተካከያ
    • JW.ORG
    • ግባ
    አጋራ