ዘሌዋውያን 11:44 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 44 እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝና፤+ እኔ ቅዱስ ስለሆንኩ+ እናንተም ራሳችሁን ልትቀድሱና ቅዱስ ልትሆኑ ይገባል።+ በምድር ላይ በሚንቀሳቀስ በማንኛውም የሚርመሰመስ ፍጥረት ራሳችሁን* አታርክሱ። ዘዳግም 7:6 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 6 ምክንያቱም አንተ ለአምላክህ ለይሖዋ ቅዱስ ሕዝብ ነህ፤ አምላክህ ይሖዋ በምድር ላይ ካሉ ሕዝቦች ሁሉ መካከል አንተን የራሱ ሕዝብ፣ ልዩ ንብረቱ* እንድትሆን መርጦሃል።+ 1 ጴጥሮስ 2:9 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 እናንተ ግን ከጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃኑ የጠራችሁን+ የእሱን “ድንቅ ባሕርያት* በየቦታው እንድታውጁ+ የተመረጠ ዘር፣ ንጉሣዊ ካህናት፣ ቅዱስ ብሔር፣+ ልዩ ንብረት እንዲሆን የተለየ ሕዝብ”+ ናችሁ። ራእይ 5:9, 10 አዲስ ዓለም ትርጉም መጽሐፍ ቅዱስ 9 እንዲህም እያሉ አዲስ መዝሙር ዘመሩ፦+ “ጥቅልሉን ልትወስድና ማኅተሞቹን ልትከፍት ይገባሃል፤ ታርደሃልና፤ በደምህም ከየነገዱ፣ ከየቋንቋው፣ ከየሕዝቡና ከየብሔሩ+ ሰዎችን ለአምላክ ዋጅተሃል፤+ 10 እንዲሁም ለአምላካችን መንግሥትና+ ካህናት እንዲሆኑ አድርገሃቸዋል፤+ በምድርም ላይ ነገሥታት ሆነው ይገዛሉ።”+
44 እኔ አምላካችሁ ይሖዋ ነኝና፤+ እኔ ቅዱስ ስለሆንኩ+ እናንተም ራሳችሁን ልትቀድሱና ቅዱስ ልትሆኑ ይገባል።+ በምድር ላይ በሚንቀሳቀስ በማንኛውም የሚርመሰመስ ፍጥረት ራሳችሁን* አታርክሱ።
6 ምክንያቱም አንተ ለአምላክህ ለይሖዋ ቅዱስ ሕዝብ ነህ፤ አምላክህ ይሖዋ በምድር ላይ ካሉ ሕዝቦች ሁሉ መካከል አንተን የራሱ ሕዝብ፣ ልዩ ንብረቱ* እንድትሆን መርጦሃል።+
9 እናንተ ግን ከጨለማ ወደ አስደናቂ ብርሃኑ የጠራችሁን+ የእሱን “ድንቅ ባሕርያት* በየቦታው እንድታውጁ+ የተመረጠ ዘር፣ ንጉሣዊ ካህናት፣ ቅዱስ ብሔር፣+ ልዩ ንብረት እንዲሆን የተለየ ሕዝብ”+ ናችሁ።
9 እንዲህም እያሉ አዲስ መዝሙር ዘመሩ፦+ “ጥቅልሉን ልትወስድና ማኅተሞቹን ልትከፍት ይገባሃል፤ ታርደሃልና፤ በደምህም ከየነገዱ፣ ከየቋንቋው፣ ከየሕዝቡና ከየብሔሩ+ ሰዎችን ለአምላክ ዋጅተሃል፤+ 10 እንዲሁም ለአምላካችን መንግሥትና+ ካህናት እንዲሆኑ አድርገሃቸዋል፤+ በምድርም ላይ ነገሥታት ሆነው ይገዛሉ።”+